የኢትዮጵያ የመሠረተ ልማት አዲስ ምዕራፍ

Date:

ኢትዮጵያ ባለፉት አምስት ዓመታት በመሠረተ ልማትና በታዳሽ ኃይል ልማት ረገድ ያስመዘገበችው ውጤት ተስፋ ሰጪ መሆኑን የከተማና የመሠረተ ልማት ሚኒስቴር ይፋ አድርጓል።

በዚህም መሠረት የሀገሪቱ የታዳሽ ኃይል የማመንጨት አቅም ከነበረበት 4 ሺህ 478 ሜጋ ዋት ወደ 9 ሺህ 554 ሜጋ ዋት ከፍ እንዲል የተደረገ ሲሆን፣ የመንገድ ርዝመትም በ40 ሺህ ኪሎ ሜትር አዳዲስ ግንባታዎች ታግዞ ከ44 ሺህ ወደ 182 ሺህ ኪሎ ሜትር አድጓል።

ይህንን አገራዊ ስኬትና የዘርፉን የወደፊት አቅጣጫ ይበልጥ ለማሳየትም “ኢትዮጵያ ትገነባለች! ፈጠራ፣ ፍጥነት እና ጥራት ለመሰረተ ልማት እመርታ” በሚል መሪ ቃል ከሚያዚያ 9 እስከ 12 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ሴንተር “የኢትዮጵያ የመሠረተ ልማትና ኮንስትራክሽን ሳምንት” ይካሄዳል።

መድረኩ የሀገር ውስጥና የውጭ የኢንዱስትሪ ተዋናዮች፣ የፈጠራ ባለቤቶችና የግንባታ ግብአት አቅራቢዎች የሚገናኙበት ከመሆኑም በላይ፣ ከግንባታ ማሽነሪዎች እስከ ዘመናዊ ዲጂታል ቴክኖሎጂዎች የሚቀርቡበት በመሆኑ የዘርፉን ግብይትና የልምድ ልውውጥ በከፍተኛ ደረጃ ያነቃቃል ተብሎ ይጠበቃል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አበባው ደሳለው (ዶ/ር) ከማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲና ተሳትፎ ራሳቸውን አገለሉ

የቀድሞው የተወካዮች ምክር ቤት አባልና የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን)...

ኢትዮጵያ በወጣቶች ኦሊምፒክ አራተኛዋን የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች

በሴኔጋል ዋና ከተማ ዳካር እየተካሄደ ባለው አራተኛው የወጣቶች ኦሊምፒክ...

በወራቤ ሆስፒታል የተመረቀው የኦክስጅን ፋብሪካ በሰዓት 60 ኪዩቢክ ሜትር የማምረት አቅም እንዳለው ተገለጸ

በወራቤ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የተመረቀው የኦክስጅን ማምረቻ ፋብሪካ በሰዓት...