የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ስድስት ወራት ውስጥ በሕገ-ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የተገኘ 8,183 ሊትር ነዳጅ መወረሱን አስታወቀ።
በከተማዋ ብቻ በተካሄደው በዚህ የቁጥጥር ስራ በውሃ ኮዳና ባልተፈቀዱ እቃዎች ሲጓጓዙ ከተያዙት ውስጥ 5,900 ሊትሩ ናፍጣ ሲሆን፣ ቀሪው ከ2,000 ሊትር በላይ ቤንዚንና ነጭ ጋዝ መሆኑ ተገልጿል።
ቢሮው በከተማዋ በሚገኙ ማደያዎች ላይ ጥብቅ ክትትል እያደረገ መሆኑን ጠቅሶ፣ ነዳጅ እያላቸው “የለንም” በሚሉና አገልግሎት በሚያቋርጡ ነጋዴዎች ላይ አስተዳደራዊና ሕጋዊ እርምጃዎችን እየወሰደ ይገኛል። በዚህም መሠረት ባለፉት ስድስት ወራት ነዳጅ ደብቀው የተገኙ ሦስት ማደያዎች ላይ ክስ ተመስርቶ የታሸጉ ሲሆን፣ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያም ተሰጥቷቸዋል።
ቢሮው አክሎም “ጀነሬተር የለኝም” ወይም “መቅጃ ተበላሸ” በሚሉ ምክንያቶች አገልግሎት ማቋረጥ እንደማይቻልና ቁጥጥሩ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አሳስቧል።
8,183 ሊትር ነዳጅ ተወረሰ
Date:
