ተወዳጅዋ አርቲስት አስለፈች በቀለ ከልጅነቷ ጀምሮ በጡረታ እረፍት እስከተገለለችበት ጊዜ ድረስ በኢትዮጽያ ብሔራዊ ቴአትር በባህል ሙዚቃና በቴአትር ዘርፍ ደከመኝ ፣ሰለቸኝ ሳትል ያገለገለች ታላቅ አርቲስት ስትሆን በኢትዮጽያ የኪነ ጥበብ ታሪክ ደማቅ አሻራዋን እሳርፋለች።
ይህች ታላቅ የኪነጥበብ ሰው በመላው ሀገሪቱ እና በተለያዩ የውጭ ሀገራት በመጓዝ በባህልና ኪነጥበብ ዘርፍ የሀገርዋን ገጽታ የገነባች ፣ሀገርዋን ለዓለም ያስተዋወቀች የዘርፉ ጀግና እንስት ነበረች።
እርቲስት አሰለፈች በቀለ በሀገረ አሜሩካ መጋቢት 10 ቀን 2018 ዓ/ም ከዚህ ዓለም ድካም ያረፈች ሲሆን በመጪው ሳምንት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ቤተስቦችዋ፣የሥራ ባልደረቦችዋ ፣አድናቂዎችዋ በተገኙበት የእስከሬን ሽኝት ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል።
ለቤተስቦችዋ፣ ለባልደረቦችዋ፣ለወዳጅ ዘመዶችዋ ፣ለመላው ሕዝብ መጽናናት ይሁን።
ነፍስ ይማር
