የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ ለዓለም ዋንጫ የሎተሪ ዕጣ አዘጋጀ

Date:

የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ ከVISA ጋር በመሆን በሰሜን አሜሪካ በሚካሄደው የዓለም ዋንጫ ላይ በተመልካችነት ለመሳተፍ የሚያስችል ዕጣ የሚያስገኘውን “ጉዞ ወደ ፊፋ የዓለም ዋንጫ 2026” ዘመቻ በይፋ አስጀምሯል።

ዕጣው በካርዱ ግብይት ለሚፈጽሙ የኮፕ VISA ካርድ ደንበኞች የዕጩነት የዕጣ ቁጥር በማደል ዕድለኛ ለሚሆኑ ሁለት፥ ደንበኞች እያንዳንዳቸው በአንድ ተጨማሪ ሰው ታጅበው ቪዛ፣ የደርሶ መልስ የአየር ትኬት፣ ሆቴልና ምግብ፣ የጨዋታ ትኬቶችና ተዛማጅ ወጪዎችን ያካተተ ሙሉ ፓኬጅ ያስገኛል ተብሏል።

በዕጣው ብቁ የሚያደርጉ ግብይቶችም፥ በቪዛ ክላሲክ ዴቢት ካርዶች የተከናወኑ የሀገር ውስጥ ፖስ እና የኢ-ኮሜርስ ክፍያዎች(በመደበኛና በኮፕባንክ አልሁዳ) የሚከናወኑ ግብይቶች፣ በቪዛ ክላሲክ ፕሪ ፔይድ ካርዶች የሚፈጸሙ ዓለም አቀፍና ኦንላይን ክፍያዎች፣ በቪዛ ፕላቲኒየም ፕሪ ፔይድ ካርዶች የሚከናወኑ ፕሪሚየም ዓለም አቀፍ ግብይቶችና በሁሉም ምድቦች የሚከናወኑ ‘ኮንታክትለስ’ ክፍያዎች መሆናቸውንም አስታውቋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

30 ሺህ ተሳታፊዎችን የሚያስተናግደው ዓለማ አቀፍ የጤና ጉባኤ ሊካሄድ ነው

የዲፕሎማሲ መዲናዋ አዲስ አበባ 5ኛውን ዓለም አቀፍ የአፍሪካ የሕዝብ...

የመማሪያ ማስተማሪያ መጻህፍት እጥረትን ለማሟላት በትኩረት እየተሰራ ነዉ

የትምህርት ጥራቱን የበለጠ ለማሻሻል የቅድመ አንደኛና የመጀመሪያ ደረጃ የመማሪያ...

የፊንቴክ ሥራ አስኪያጅ በከባድ የማታለል ወንጀል ተከሰሰ

​በአዲስ አበባ የፊንቴክ ኢንቨስትመንት ሥራ አስኪያጅ የሆኑት ዳንኤል ዮሐንስ፣...

ኢራን በሆርሙዝ በኩል ሊያልፉ የነበሩ ሦስት መርከቦችን መመለሷን አሳወቀች

የኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ ዛሬ ጠዋት በሆርሙዝ ወሽመጥ በኩል...