የዳንጎቴ ነዳጅ ማጣሪያ የአክሲዮን ሽያጭ

Date:

የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን የዳንጎቴ የነዳጅ ማጣሪያ ኩባንያ አክሲዮኖች ሽያጭን በተመለከተ ይፋዊ ማስታወቂያ አዉጥቷል። ባለስልጣኑ እንዳስታወቀው የአንድ አክሲዮን የመግዣ ዋጋ 74 ነጥብ 9 ብር ሲሆን፣ የሽያጭ ሂደቱም እስከ ጥቅምት 13 ቀን 2019 ዓ.ም ድረስ ብቻ ይቆያል።

ይህ የአክሲዮን ሽያጭ ከፍተኛ የሀብት መጠን ላላቸው ባለሀብቶች የተዘጋጀ መሆኑ ተገልጿል። በዚህም መሰረት መስፈርቱን አሟልተው አክሲዮኖቹን መግዛት የሚችሉት፣ አንድ ተሽከርካሪ እና አንድ የመኖሪያ ቤት ሳይጨምር ቢያንስ 10 ሚሊዮን ብር የተጣራ ሀብት ያላቸው ባለሀብቶች እንደሆኑ ተብራርቷል።

እነዚህን መስፈርቶች የሚያሟሉ እና የአክሲዮን ግዢ ለመፈጸም ፍላጎት ያላቸው አካላት፣ አክሲዮኖችን የመሸጥ እና የመግዛት ህጋዊ ፈቃድ በተሰጣቸው ድርጅቶች በኩል ሂደቱን ማከናወን እንደሚችሉ ባለስልጣኑ አሳውቋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በሆርሙዝ አቅራቢያ ሁለት መርከቦች ጥቃት ከተፈጸመባቸው በኋላ መስመጣቸው ተነገረ

የባሕር ትራንስፖርት ባለሥልጣናት እንዳስታወቁት ባለፉት አስር ቀናት በወሽመጡ ላይ...

የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ከመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ጋር እንዲወዳደሩ ቢፈለግም ሊሳካላቸው አልቻለም

የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ከመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ጋር እንዲወዳደሩ ቢፈለግም...

‹‹ሕገመንግሥታዊ ተቃርኖዎች››   ያራቆተው የተቃርኖ ገመና

በደረጀ ይመር   ማስፈንጠሪያ ግዮን መጽሔት :-    የአብርሆት ዘመን ፍሬ የሆነው...

የኢትዮጵያ እና የቻይና አየር መንገዶች የጋራ ስምምነት ተፈራረሙ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና ቻይና ሳውዘርን አየር መንገድ በቻይና...