የግራሚ መድረክ ወይንስ የፖለቲካ አውድማ? የትራምፕ አስተዳደር እና የኪነ-ጥበብ ሰዎች ፍጥጫ

Date:

የ2026 የግራሚ የሽልማት ምሽት ከዜማ ይልቅ የፖለቲካ ንዝረት የበረከተበት ሆኖ በታሪክ ተመዝግቦ አልፏል።

የሎስ አንጀለሱ የክሪፕቶ ዶት ኮም አሬና መድረክ፣ በዋሽንግተን ካለው ዋይት ሀውስ ጋር በግልጽ ጦርነት የገጠመበትና የሙዚቃውን ዓለም ለሁለት የከፈለ ትዕይንት አስተናግዷል።

ምሽቱን በከፍተኛ ተቃውሞ ካደመቁት መካከል የፖርቶሪኮዉ የራፕ ንጉሥ ባድ በኒ (Bad Bunny) ቀዳሚውን ስፍራ ይይዛል።
“የዓመቱ ምርጥ የከተማ ሙዚቃ” ሽልማቱን ለመቀበል ወደ መድረክ በወጣበት ወቅት፣ የደስታ ስሜት ሳይሆን የሚታይበት ቁጣ ነበር።

ባድ በኒ የአሜሪካን የስደተኞች ጉዳይ አስፈፃሚ አካል (ICE) በቀጥታ በማውገዝ፤‹‹እኛ ባዕዳን አይደለንም፤ እኛ ሰዎች ነን፣ እኛ አሜሪካውያን ነን! ICE ይውጣ!››ሲል ያሰማው ድምፅ በአዳራሹ የነበረውን ድባብ በአንድ ጊዜ ቀይሮታል።

ይህ ተቃውሞ በቅርቡ በሚኒያፖሊስ በፌዴራል ወኪሎች እጅ የተገደሉትን ሁለት ዜጎች ተከትሎ በሀገሪቱ እየተቀጣጠለ ካለው ተቃውሞ ጋር የተያያዘ ነው።

በተመሳሳይ ዝነኛዋ ቢሊ አይሊሽ (Billie Eilish) በልብሷ ላይ “ICE out” የሚል አርማ በማድረግና‹‹በተሰረቀ መሬት ላይ ማንም ህገ-ወጥ ስደተኛ የለም›› በማለት የትራምፕን ጠንካራ የስደተኞች ፖሊሲ በይፋ ተገዳድራለች።

በሌላኛው ጽንፍ ደግሞ የራፕ ንግሥቷ ኒኪ ሚናጅ ከትራምፕ አስተዳደር ጋር ያሳየችው መቀራረብ የብዙዎችን ቅንድብ በግርምት ከፍ ያስደረገ ነበር አስነስቷል።

በግራሚ ምሽት ላይ ያልተገኘችው ኒኪ፤ባለፈው ሳምንት በዋይት ሀውስ ተገኝታ ከፕሬዝዳንት ትራምፕ ጋር በጋራ መታየቷ ይታወሳል።

ትራምፕ ኒኪን ‹‹በታሪክ ታላቋ እና ስኬታማዋ ሴት የራፕ ተጫዋች››ሲሉ ማወደሳቸው፤ አስተዳደሩ በኪነ-ጥበብ ዓለም ውስጥ ተፅዕኖ ፈጣሪዎችን በመጠቀም የፖለቲካ ድጋፍ ለማሰባሰብ እያደረገ ያለው ስልታዊ እርምጃ ተደርጎ ተወስዷል።

የግራሚው መድረክ አስተናባሪ ትሬቨር ኖሃ፤ ይህንን ሁኔታ በፈገግታ የታጀበ ቀልድ ቢያቀርበውም ከጀርባው ግን የሙዚቃው ኢንዱስትሪ ለሁለት መከፈሉን የሚያሳይ ትልቅ እውነት ነበረው።

የዘንድሮው የግራሚ ምሽት አርቲስቶች ከሙዚቃ ባለፈ የፖለቲካ ተዋናይ እየሆኑ መመጣታቸውን ያረጋገጠ ነው።

በአንድ በኩል ለሰብዓዊ መብትና ለፍትህ የቆሙት እንደ ባድ በኒ ያሉ አርቲስቶች፣ በሌላ በኩል ደግሞ ከመንግስት ጋር በመወዳጀት “የጥቅም ዲፕሎማሲ” የመረጡት እንደ ኒኪ ሚናጅ ያሉ ተዋናዮች በግልጽ ታይተዋል።

ይህ የኪነ-ጥበብ ሰዎች ፍጭት፤በትራምፕ ሁለተኛ ዘመነ መንግስት የአሜሪካ ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ መሰረት ምን ያህል እየተናወጠ መሆኑን የሚያሳይ ትልቅ ማሳያ ሆኖ አልፏል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የአንጋፋውን ጋዜጠኛ ድምጽ እንደገና እንስማ

ኑ ጥቂት ድጋፍ አድርገን ተስፋ እናለምልም ‼️ ባለ ወርቃማ ድምጹ...

ግዮን መጽሔት ዛሬ ቅዳሜ መስከረም 9 2019 ዓ.ም ገበያ ላይ ውሏል !!!

-የግዮን እንግዳ አምዳችን :- ‹‹ምንጩና ጸሐፊው በማይታወቅ መረጃ መመራት አደገኛ...

ሸኽ መሃመድ አል አሙዲ ተጨማሪ 40 ሺህ ሠራተኞች እንዲቀጠሩ አቅጣጫ ሰጡ

የMIDROC Investment Group ሊቀመንበር ሼክ መሃመድ ሁሴን አል...

የወርቅ ማዕድን ሠራተኛው ከመገደላቸው በፊት ቤተሰባቸው ከታጣቂዎች ጋር ያደረገው የመጨረሻው የስልክ ምልልስ

ማስጠንቀቂያ፡ ቀጥሎ የሚያነብቡት ታሪክ ሊረብሽዎት ይችላል በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ...