የ2018 ዓ.ም የጥምቀት በዓልን አስመልክቶ በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ መሪነት የአዲስ አበባና የሸገር አህጉረ ስብከት የሥራ ሐላፊዎችንና አድባራት የአገልግሎት መሪዎችችን ያካተት የምክክር ጉባኤ እየተካሄደ ይገኛል።
በጉባኤው ላይ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ፣ የሸገርና የደቡብ ምዕራብ ሸዋ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፣ ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ የአዲስ አበባና የሀዲያ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ የመንበረ ፓትርያርክ የሥራ ሐላፊዎች ።
እንዲሁም የአዲስ አበባና የሸገር አህጉረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጆች፣ የሁሉቱም አህጉረ ስብከት የዋና ክፍል ሐላፊዎች የክፍላተ ከተማ ቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጆችና የሥራ ሐላፊዎች ፣የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች ጸሐፊዎች የሰበካ ጉባኤ ምክትል ሊቃነ መናብርት፣ ሊቃነ ጠበብት ቄሰ ገበዞች ሊቃነ ዲያቆናት፣የሰንበት ትምህርት ቤቶች ሰብሳቢዎች ተገኝተዋል።
ጉባኤው በጸሎት ከተከፈተ በኋላ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የካህናት አስተዳዳር አስተባባሪነት በተዘጋጀው ጉባኤ ላይ በዶ/ር በለጠ ብርሃኑ የጥምቀት በዓል አከባበር ተግዳሮቶችና የመፍትሔ ሐሳቦች በሚል ርእስ ጥናታዊ ጽሑፍ ቀርቧል።
በጉባኤው የጥምቀት በዓል አከባበር ሥርዐተ ቤተ ክርስቲያንን መሠረት ያደረገ ወጥነት ያለው የመውጫና መግቢያ ሰዓት ጉዳይ ላይ መመሪያ እንደሚተላለፍበት ይጠበቃል።
©የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሚዲያ
