የፈጥኖ ደራሹ ኃይሎች በሱዳን ኤል-ፋሸር  በሰብአዊነት ላይ ወንጀል ፈጽመዋል

Date:

እንደ የእውነታ አፈላላጊ ኮሚሽን ሊቀመንበር መሐመድ ቻንዴ ኦስማን፣ የፈጥኖ ደራሹ ኃይሉ የፈጸማቸው ድርጊቶች የሚከተሉትን ያካትታሉ፡-

🔸 የጅምላ ግድያ፣

🔸 ፆታዊ ጥቃት፣

🔸 ዘረፋ እና

🔸 ውድመት እንዲሁም በአንዳንድ ሁኔታዎች ማንነት ላይ ያነጣጠረ ጥቃት እና ጭፍጨፋን አስከትሏል።

የተፈፀመውን በደልን ለመመርመር ኃላፊነት የተሰጠው የተባበሩት መንግሥታት ቡድን ሪፖርቱን ከ200 በሚበልጡ ቃለመጠይቆች፣ የቪዲዮ ማስረጃዎች እና ከሲቪል ድርጅቶች በደረሰው መረጃ ላይ መሠረት አድርጓል።

በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በኤል-ፋሸር፣ በሰሜን ዳርፉር የሱዳን ጦር የመጨረሻ ምሽግ እና አሁን ባለው ግጭት የፊት መስመር ላይ ከበባ ውስጥ ይገኛሉ።

“የጭካኔ ጦርነት” ተብሎ የተሰየመው ባለ 18 ገጽ ሪፖርት፣ ፈጥኖ ደራሹ ኃይሉ እና አጋሮቹ አስፈላጊ የምግብ እና የሕክምና እርዳታን በመከልከል ርሃብን እንደ ጦር መሣሪያ እየተጠቀሙበት ነው ሲል ከሷል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አበባው ደሳለው (ዶ/ር) ከማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲና ተሳትፎ ራሳቸውን አገለሉ

የቀድሞው የተወካዮች ምክር ቤት አባልና የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን)...

ኢትዮጵያ በወጣቶች ኦሊምፒክ አራተኛዋን የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች

በሴኔጋል ዋና ከተማ ዳካር እየተካሄደ ባለው አራተኛው የወጣቶች ኦሊምፒክ...

በወራቤ ሆስፒታል የተመረቀው የኦክስጅን ፋብሪካ በሰዓት 60 ኪዩቢክ ሜትር የማምረት አቅም እንዳለው ተገለጸ

በወራቤ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የተመረቀው የኦክስጅን ማምረቻ ፋብሪካ በሰዓት...