ፑቲንን ማመን አይቻልም-ቮሎዲሚር ዘለንስኪ

Date:

የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ ፤የራሺያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን  ሞስኮ ውስጥ ለመገናኘት ያቀረቡትን ሀሳብ  ውድቅ አደረጉ።

ኤቢሲ ኒውስ በተባለው የአሜሪካው መገናኛ ዘዴ ዛሬ ቅዳሜ  በተለቀቀ ቃለ ምልልስ ዘለንስኪ ኪየቭን እንደ አማራጭ ቦታ ጠቁመዋል።

ፑቲን “ወደ ኪየቭ ሊመጣ ይችላል” ያሉት ዘለንስኪ፤ ሀገራቸው ከሩሲያ ጥቃት እየደረሰባት እያለ፤ ወደ ሞስኮ መሄድ እንደማይችሉም ተናግረዋል።

የዩክሬኑ መሪ አያይዘውም ፑቲን ሞስኮ ለመገናኘት ያቀረቡት ሀሳብ ጉዳዩን ለማዝግየት እንደ ስልት የተጠቀሙበት መሆኑን ገልፀዋል።

«ወደ ሞስኮ መሄድ አልችልም … አገሬ በሚሳኤል  ስር ወድቃ እያለ እና በየቀኑ ጥቃቶች እየተፈፀሙ። ወደዚህ የሽብር ዋና ከተማ መሄድ አልችልም።የታወቀ ነው።

እና እሱም ይረዳል።»ብለዋል።ዘለንስኪ በእንግሊዥኛ ቋንቋ እንደተናገሩት ፑቲንን ማመን አይቻልም።እናም ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር «ጨዋታዎችን  እየተጫወተ ነው» ብለዋል።

የዩክሬን ፕሬዝዳንት ሩሲያ  ከየካቲት 2022 ዓ/ም ጀምሮ በሀገራቸው ላይ የምታደርገውን ጦርነት በድርድር ለማቆም ከፑቲን  ጋር ለመገናኘት ደጋግመው ጥሪ አቅርበዋል።

እንደ ዩክሬን ምንጮች በግጭቱ ውስጥ ገለልተኛ ናቸው የሚባሉ ፤ ቱርክ እና ሶስት የባሕረ ሰላጤውን ሀገራት ጨምሮ  ቢያንስ ሰባት ሀገሮች እንዲህ ዓይነቱን ስብሰባ ለማስተናገድ ጥሪ አቅርበዋል።

ያም ሆኖ ያለፈው ረቡዕ  ፑቲን፤ አዎንታዊ ውጤት እና ተስፋ  ካለ፤ ዜለንስኪ ወደ ሞስኮ ሊመጡ እንደሚችሉ ተናግረዋል።ሲል የጀርመኑ ዜና አገልግሎት ዲፒኤ ዘግቧል።

ፑቲንን ማመን አይቻልም-
ቮሎዲሚር ዘለንስኪ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አበባው ደሳለው (ዶ/ር) ከማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲና ተሳትፎ ራሳቸውን አገለሉ

የቀድሞው የተወካዮች ምክር ቤት አባልና የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን)...

ኢትዮጵያ በወጣቶች ኦሊምፒክ አራተኛዋን የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች

በሴኔጋል ዋና ከተማ ዳካር እየተካሄደ ባለው አራተኛው የወጣቶች ኦሊምፒክ...

በወራቤ ሆስፒታል የተመረቀው የኦክስጅን ፋብሪካ በሰዓት 60 ኪዩቢክ ሜትር የማምረት አቅም እንዳለው ተገለጸ

በወራቤ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የተመረቀው የኦክስጅን ማምረቻ ፋብሪካ በሰዓት...