የፑቲን እና ትራምፕ የስልክ ውይይት

Date:

ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን እና ዶናልድ ትራምፕ በስልክ ለአንድ ሰዓት ያህል በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተነጋገሩ ።

ፕሬዚዳንት ፑቲን በዩክሬን የጀመሩትን የጦረነት ዓላማ ሳያሳኩ እንደማይተውት ነግረዋቸዋል ለፕሬዚዳንት ትራምፕ ።

ለሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት ምክንያት የሆኑ ጉዳዮችን ሙሉ  ለሙሉ ሞስኮ  እንደምታጠፋ እና ይህን ሳታሳካ እንደማትቆምም በግልጽ  አስቀምጠዋል።

ፑቲን በድርድር እና በፖለቲካዊ መንገዶች ውጥረቱን ለመፍታት ፍላጎት እንዳላቸውም  የክሬምሊን ረዳት ዩሪ  ዩሻኮቭ ለጋዜጠኞች አረጋግጠዋል ።

መሪዎቹ ለአንድ ሰዓት ያህል በሩሲያ-ዩክሬን ጦርነት እና በኢራን ጉዳይ ላይ መነጋገራቸውም ተሰምቷል።

ሩሲያ በ2022 በዩክሬን ላይ ጦር ያዘመተችበት ዋነኛው ምክንያት ኪዬቭ የሰሜን አትላንቲክ የጦር ጥምረትን እና የአውሮፓ ህብረትን ልትቀላቀል ነው የሚል ስጋት ስላደረባት እንደነበር የሚዘነጋ አይደለም ።

ስድእተኛው ውይይታቸውን ያደረጉት ትራምፕ እና ፑቲን አሁንም ዲፕሎማሲያዊ መንገዶችን መከተል እንደሚያሻ በግልጽ አስቀምጠዋል ።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በአዲስ አበባ የታክስ ዕዳ ምህረት አሰጣጥን የሚያስተዳድር አዲስ ረቂቅ መመሪያ ወጣ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ቢሮ፣ በተለያዩ ከግብር ከፋዮች...

እግዚአብሔር የሰጠኝን ተልዕኮዎች ፈጽሜያለሁ የአዛዥነት ዘመኔ እያበቃ ነው

የኡጋንዳ የመከላከያ ኃይሎች አዛዥ (CDF) ጄነራል ሙሁዚ ካይኔሩጋባ ከወታደራዊ...

አሐዱ ባንክ 1ነጥብ 07 ቢሊዮን ብር አተረፈ

ባንኩ በተጠናቀቀው የሂሳብ ዓመት ከ3 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር...

በጋምቤላ ከምሽት አንድ ሰዓት በኋላ ነዋሪዎች እንዳይንቀሳቀሱ ተከለከለ

ከጋምቤላ ክልል ዋና ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘው ጋምቤላ...