የ4ቱ የፖለቲካ ፓርቲዎች ማኒፌስቶ በዚህ ሳምንት ይፋ ይደረጋል

Date:

የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ (ኢህአፓ)፣ የመላው ኢትዮጵያ አብዮታዊ ድርጅት (መኢአድ)፣ አማራ ግዮናዊ ንቅናቄ (አግን) እንዲሁም እናት ፓርቲ የመሰረቱት ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት ጥረምረቱ ውስጥ በሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች በጋራ የተዘጋጀው የምርጫ መመሪያ መርሃ-ግብር ወይም ማኒፌስቶ በዚህ ሳምንት ይፋ እንደሚያደርግ ተገልጾአል።   

የትብብሩ ዋና ጸሐፊ ሚስጥረ ሥላሴ ታምራት ከአሐዱ ራድዮ “ልሳነ ምርጫ” ዝግጅት ጋር በነበራቸው ቆይታ፡ ሰነዱ በጥምረቱ ውስጥ ያሉ ፓርቲዎችን በሚያስማሙ ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ ትኩረት ያደረገ ነው።

‘ማኒፌስቶው’ “ኢትዮጵያ ምን መሆን አለባት?” የሚለውን መሠረታዊ ጥያቄ የሚመልስና ወደፊት ሊቀረጹ ስለሚገባቸው ፖሊሲዎች አቅጣጫ የሚያሳይ እንደሆነ ጠቁመዋል።

ሰነዱ የተዘጋጀው በፓርቲዎቹ መካከል ያሉ የሐሳብ ልዩነቶችን በማሰባጠርና የጋራ አቋሞችን በማጠናከር እንደሆነም ተገልጿል።

ጥምረቱ ካዘጋጀው ማኒፌስቶ በተጨማሪ፣ ለ7ኛው አገራዊ ምርጫ መሟላት ያለባቸውን ቅድመ ሁኔታዎች አስቀምጧል።

ከእነዚህም መካከል የዴሞክራሲ ተቋማት ገለልተኝነት፣ የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱና በሀገሪቱ የሚታዩ ግጭቶች በአስቸኳይ እንዲቆሙ የሚሉ ነጥቦች ዋና ዋናዎቹ መሆናቸውን ሚስጥረ ሥላሴ ታምራት ለአሐዱ ተናግረዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እግዚአብሔር የሰጠኝን ተልዕኮዎች ፈጽሜያለሁ የአዛዥነት ዘመኔ እያበቃ ነው

የኡጋንዳ የመከላከያ ኃይሎች አዛዥ (CDF) ጄነራል ሙሁዚ ካይኔሩጋባ ከወታደራዊ...

አሐዱ ባንክ 1ነጥብ 07 ቢሊዮን ብር አተረፈ

ባንኩ በተጠናቀቀው የሂሳብ ዓመት ከ3 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር...

በጋምቤላ ከምሽት አንድ ሰዓት በኋላ ነዋሪዎች እንዳይንቀሳቀሱ ተከለከለ

ከጋምቤላ ክልል ዋና ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘው ጋምቤላ...

ፍልውሃ እና ሶደሬ!

ከሐዉለት አህመድ በቀደም ከብዙ ዓመታት በኋላ የፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት ሔጄ...