ዩጋንዳ በቀጣዩ ዓመት መጀመሪያ የአለም አዲስ የነዳጅ ላኪ ሀገር ልትሆን ነው

Date:

ዩጋንዳ በፈረንጆቹ 2027 መጀመሪያ ላይ ከአልበርቲን ግራበን ማዕድን ማውጫ የሚወጣውን “ፐርል ስዊት” የተሰኘ ድፍድፍ የነዳጅ ዘይት ለዓለም ገበያ በማቅረብ አዲስ የነዳጅ ላኪ ሀገር ትሆናለች ተብሎ ይጠበቃል።

የዩጋንዳ ብሔራዊ የነዳጅ ኩባንያ ነዳጁን ለዓለም ገበያ ለማስተዋወቅ ዓለም አቀፍ የኢነርጂ ንግድ ድርጅት ከሆኑት ቪቶል ጋር ተዋውሏል። በፈረንሳይ ግዙፉ የኢነርጂ ኩባንያ የሆነዉ ቶታል ኢነርጂስ  እና በቻይናው ሲኤንኦኦሲ እየተከናወኑ ካሉት የቲሌንጋ እና ኪንግፊሸር የነዳጅ ማልማት ፕሮጀክቶች የሚመነጨው ይህ የነዳጅ ዘይት፣ ዝቅተኛ ሰልፈር ያለው እና ጥራቱን የጠበቀ መሆኑ ተገልጿል።

ምርት ወደ ዓለም ገበያ ለማድረስ ታንዛኒያ ውስጥ ወዳለው የታንጋ ወደብ የሚዘልቀው የ1,443 ኪሎ ሜትር ምስራቅ አፍሪካ የድፍድፍ ነዳጅ ዘይት ቧንቧ መስመር ግንባታ ከ90 በመቶ በላይ ተጠናቋል። በ5 ቢሊዮን ዶላር ወጪ እየተገነባ ያለው ይህ የቧንቧ መስመር በቀን ከ200 ሺህ እስከ 246 ሺህ  በርሜል የነዳጅ ዘይት የማጓጓዝ አቅም እንዳለው ተጠቁሟል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በጋምቤላ ከምሽት አንድ ሰዓት በኋላ ነዋሪዎች እንዳይንቀሳቀሱ ተከለከለ

ከጋምቤላ ክልል ዋና ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘው ጋምቤላ...

ፍልውሃ እና ሶደሬ!

ከሐዉለት አህመድ በቀደም ከብዙ ዓመታት በኋላ የፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት ሔጄ...

የተጀመሩ የትምህርት ሪፎርሞችን በጽኑ መሠረት ላይ ለማቆም በቁርጠኝነት መስራት ይገባል

የትምህርት ሚኒስቴር አመራሮችና ሠራተኞች የ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያውን ሩብ...

የአዉሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ የቡና ገበያ መዳረሻዎች እየፈለገ ነዉ

በፈረንጆቹ 2023 የፀደቀው የአውሮፓ ህብረት የደን ጭፍጨፋ ህግ ምርቶች...