ዳሸን እና ንግድ ባንክ አዲስ አማራጭ አምጥተዋል

Date:

ዳሽን ባንክና ንግድ ባንክ ወደ ትግበራ ያስገቡት አዲስ የሀዋላ መላኪያ አማራጭ ወይም ፕላትፎርም ዛሬ ነሀሴ 202017 በይፋ ተዋውቋል።

ሁለቱ ባንኮች ላኪዎችና ተቀባዮች በቀላል መንገድ የሀዋላ ልውውጥ የሚያደርጉበትን አዲስ የሀዋላ መላኪያ አማራጭ ፕላትፎርም አስተዋውቀዋል።

ይህንን አዲስ የሀዋላ መላላኪያ አማራጭ ያበለፀገው ኤግል ላይንስ ሲስተም ነው።

የውጭ ምንዛሬ ፍሰት በሚፈለገው ደረጃ እንዲደርስ ባንኮቻችን ብዙ መሥራት እንደሚጠበቅባቸው የዕለቱ እንግደሠ የብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምህረቱ ተናግረዋል።

የውጭ ምንዛሪ ፍሰቱ አገሪቱ በምትፈልገው መጠን እየመጣ ያልሆነበት ምክንያት ባንኮቻችን ለላኪዎችና ለተቀባዮች አመቺ የሆነ የዲጂታል ረመታንስ አማራጭ ስለሌላቸው መሆኑንም ተናግረዋል።

የብሔራዊ ባንክ ገዥ ሁሉም ባንኮች ህጋዊ የውጭ ምንዛሬ ወደ ሀገሪቱ የፋይናንስ ዘርፍ እንዲገባ በዲጂታል የተደገፈ የሀዋላ አማራጭ እንዲያቀርቡ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

ሁለቱ ባንኮች ያበለጸጉት አይነት ህጋዊና በቴክኖሎጂ የታገዘ ቀላል የሀዋላ ማስተላለፍያ አማራጭ ሌሎች ባንኮችም እንዲተገብሩ ዋና ገዥ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ባንኮቻችን ለላኪዎችና ለተቀባዮች አመቺ የሀዋላ ማስተላለፍያ ባለማስፋታቸው የተነሳ የውጭ ምንዛሬ በምንፈልገው ደረጃ ልናገኝ አልቻልም ብለዋል።

የውጭ ምንዛሬ ፍሰት ለማሳደግ ገንዘብ በህጋዊ የባንክ ሥርአት ለማስተላለፍ ደህንነቱ የተጠበቀ ቴክኖሎጂና የታወቁ የአገልግሎት አቅራቢዎችን በመጠቀም የውጭ ሀዋላ በፍጥነት እንዲደርስ ከማስቻሉም ባሻገር ለሀገር ኤኮኖሚ እድገት አስፈላጊም ነው ብለዋል።

ሁሉም ባንኮች ተወዳዳሪ ዋጋ ከመስጠት በተጨማሪ ለላኪዎችና ለተቀባዮች ቀላልና ግልጽ የሃዋላ ማስተላለፍያ አማራጮች ማበልጸግ ይገባቸዋል ነው ያሉት።

ውጭ ሀገር ያሉ ኢትዮጵያዊያን ወደ ኢትዮጵያ በህጋዊ መንገድ ገንዘብ ለመላክ እየፈልጉ ባንኮች አመቺና አማራጭ የሆነ የሃዋላ መላኪያ አማራጭ እያቀረቡ አለመሆኑም ተናግረዋል።

ባሁኑ ሰአት የኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሬ ተረጋግቷል ያሉት ዋና ገዢው ባንኮቻችን ይህንን ሁኔታ ስር እንዲይዝ ነገ ዛሬ ሳይሉ በቴክኖሎጂ የታገዘ የሀዋላ መላኪያ አማራጮችን ማበልፀግ ይገባቸዋል ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እግዚአብሔር የሰጠኝን ተልዕኮዎች ፈጽሜያለሁ የአዛዥነት ዘመኔ እያበቃ ነው

የኡጋንዳ የመከላከያ ኃይሎች አዛዥ (CDF) ጄነራል ሙሁዚ ካይኔሩጋባ ከወታደራዊ...

አሐዱ ባንክ 1ነጥብ 07 ቢሊዮን ብር አተረፈ

ባንኩ በተጠናቀቀው የሂሳብ ዓመት ከ3 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር...

በጋምቤላ ከምሽት አንድ ሰዓት በኋላ ነዋሪዎች እንዳይንቀሳቀሱ ተከለከለ

ከጋምቤላ ክልል ዋና ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘው ጋምቤላ...

ፍልውሃ እና ሶደሬ!

ከሐዉለት አህመድ በቀደም ከብዙ ዓመታት በኋላ የፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት ሔጄ...