ድምፃዊት ቬሮኒካ አዳነ በሰይፉ ሾው ምን አለች?

Date:

★ ይኼንን ሁሉ አዋርድ እግዚአብሔር ነው የሰጠኝ።

★ ተሸልሜ ስመጣ አባቴ አቀባበል ሲያደርግልኝ አለምን
የጨበጠ ነው የሚመስለው።

★ በቅርቡ ሃምሳ አምስት ሺህ ዳላር ካሸነፍኩኝ ግማሹን
ገንዘብ ለቤተክርስቲያን እሰጣለሁ።

★ ከዚህ በኋላ ክለብ የምሰራ አይመስለኝም።
ሴት ስትሆን ፈተናው ብዙ ነው። በጣም ነው
የሚከብደው።

★ ባለፈው ስለሪሃና የጻፍኩት በውስጥ መስመር እየመጡ
ሲፅፉልን ሙድ እንደያዙብኝ አውቄ ነው የጻፍኩት።

★ ሪሃና ዛሬ ከባሏ ጋር ኒውዮርክ ታይታ ነበር።
ደህና ነች። አታስቡ።

★ እንደ ክሪስ ብራውን አይነት ኤክስ ነበረኝ። አሁን ደግሞ
ከሱ የበለጠ ባል ይሰጠኛል።

★ በአሁኑ ሰዓት ፍቅረኛ የለኝም።

★ ብዙ ሰው ተጋብቶ ተፋቷል። እግዚአብሔር ሲፈቅድ
አገባለሁ።

★ ካገባሁኝ መፍታት አልፈልግም።

★ ድምፃዊ ሮቤል ሚደቅሳ በጣም ምርጥ ድምፅ
ያለው ልጅ ነው።

★ ከፋሲካ በኋላ ኮንሠርት ይኖረኛል።
ሙሉ ኢትዮጵያን እዞራለሁ። ኮንሠርት በጣም
ናፍቆኛል።

★ ኮንሠርቱን ከቫርዳስ ክለብ ባለቤት ተስፉ
ጋር ነው አብረን የምንሰራው።

★ እግር ኳስ የማንም ደጋፊ አይደለሁም።

★ አሁን የሰራሁት ፊልም ሁለተኛ ፊልሜ ነው።

★ ትወና ደስ ይላል። ይፈትናል። ባለፈው ከሰራሁት
በብዙ ተሽዬ ነው የመጣሁት።

★ ፊልሙን ፕሮዲውስ ያደረገው ቲክቶከሩ ጆጆ ነው።
ከአራት እስከ አምስት ሚሊዮን ብር አውጥቶበታል።

★ ፊልም ቀረጻ በጣም ድካም አለው። ኮሜዲያን
ደረጀ ሀይሌ በቀረጻው ወቅት በጣም ያስቀኝ ነበር።
ደረጀ ከኛ ከታናናሾቹ ጋር ሲሰራ ለእኛ ትልቅ
ክብር አለው።

★ ፊልሙ ስራ ላይ የሌላ ሰው ስራ ካልሰራሁ ብዬ
የወደቅሁበት አጋጣሚ ነበር።

★ በእምነቴ ሴንሴቲቭ ነኝ።

★ ሙዚቃ ቤተሰቤን የማስተዳድርበት ሙያ ነው።
እግዚአብሔር ሲፈቅድ ይኼንን ሙያ ትቼ ፈጣሪን
ባገለግለው ደስ ይለኛል።

★ ሁልጊዜም በመድሃኒዓለም እርዳታ ነው ያለሁት።

★ ብዙ ጊዜ ሰው እየጎዳኝ እያየሁ አልፋለሁ።
ክፋትና ምቀኝነት በጣም ቀላል ነው።
የማልፋቸው ነገሮች እየጎዱኝ መጡ።

★ ከተዋናይ ሙሉዓለም ጌታቸው ጋር ተያይዞ
በተወራብኝ ወሬ ክስ መስርቻለሁ።ጉዳዩን
ሕግ ይዞታል። ብዙ ማውራት አልፈልግም።

★ ከ30 ሚሊዮን በላይ ተከታይ ያለው አለምአቀፍ
ትልቅ አርቲስት ጋር ኮላብ እናድርግ አልኩት።
እሺ አለ እና ሌላ ነገር ፈልጎ ቤብ ማለት ጀመረ።
የሆነ አዋርድ ዝግጅት ላይ ሄጄ አገኘሁት።
ከዛ ሩም ቀጠረኝ። አዝኜ ተውኩት። አለቀስኩኝ።

★ አሁን ከሌላ የምወደው ጨዋ አለምአቀፍ አርቲስት
ጋር እየሰራሁ ነው።

★ ግራሚ አዋርድ ላይ የመጀመሪያውን ዙር አልፌ ነበር።
ከዛ በኋላ ውስጥ ለውስጥ ቮት ስለሚያደርጉ
ሁለተኛው ዙር ተበላሸብኝ።

★ ሽልማት የተሸለምኩኝ ጊዜ አንዲት ትልቅ
ሪልስቴት ውስጥ የምትሰራ ልጅ መጣችና
እኛ ጋር ነይ ቤት እኝሸልምሻለን አለችኝ።

★ እህቴ ሄዳ ስትጠይቃቸው ኸረ እኛ ለቪው ብለን
ነው አሏት።

★ በርሜል ጊዮርጊስ ፀበል ከሄድኩ በኋላ በሚገርም
በረከት ተሞልቻለሁ።

★ አፍሪካ ዩኒየን የተጋበዝኩት ብራንድ አምባሳደር
ስለምሆን ከነሱ ጋር ትልቅ ስራ እየሰራን ስለሆነ ነው።

★ አውሮፓ ባደረግሁት የኮንሠርት ቱር በጣም ደስ
የሚል ጊዜ አሳልፌ ነው የመጣሁት።

★ በህይወቴ ማኔጀር ኖሮኝ አያውቅም። ራሴ ነኝ የራሴ
ማኔጀር። የሚያግዘኝ ረዳት አለኝ። ሞገስ ይባላል።
እህቴ ደግሞ ቱር ማኔጀሬ ናት።
የራሴ የሆነ ዳጊ የሚባል ፎቶግራፈር አለኝ።
አሁን ወደ ቪዲዮግራፈር አድጓል።

★ ቪዛ ሁለት ጊዜ ተከልክዬ አውቃለሁ። በሶስተኛው
ነው የተሰጠኝ።

★ ከሾው በፊት ገንዘብ እጠይቃለሁ። እሱን
ካልከፈሉኝ አልሰራም።

★ ዞዲያግ የተሰኙት አልበሜን የገዙኝ ህይወቴን
አስተካክለውታል። ቤት የመግዛቴ ምስጢር
ናቸው።

★ በፊት በጣም አኩራፊ ነበርኩኝ። አሁን እድሜዬ
ስለጨመረ ነው መሰለኝ አላኮርፍም። ትቻለሁ።

★ እመቤቴ ቅድስት ድንግል ማርያምን አመሰግናለሁ።
በጣም ነው የምወዳት።
ጌታችን መድታኒታችን እየሱስ ክርስቶስን አመሰግናለሁ።
አባቴ አዳነን እና እህቴ ፍሬን አመሰግናለሁ።

★ ሰይፉ አንተ እኔ ህይወት ላይ ብዙ አሻራ አለህ።
በጣም ነው የማመሰግንህ።
እግዚአብሔር ያክብርህ።
ወደፊት በትልቅ ነገር እክስሃለሁ።

Veronica Adane አፍሪካ ውስጥ የተዘጋጁትን አዋርዶች
ጠራርገሽ በማሸነፍሽ እንኳን ደስ አለሽ።
ወደፊት ደግሞ ግራሚ አዋርድ እንድታሸንፊ
መልካም ምኞቴን እገልፅልሻለሁ።

አክባሪሽና አድናቂሽ
ዘሪሁን ተዝናኑ
ሞቅ ካለ የሚነበብ ፊርማ ጋር !!!

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

30 ሺህ ተሳታፊዎችን የሚያስተናግደው ዓለማ አቀፍ የጤና ጉባኤ ሊካሄድ ነው

የዲፕሎማሲ መዲናዋ አዲስ አበባ 5ኛውን ዓለም አቀፍ የአፍሪካ የሕዝብ...

የመማሪያ ማስተማሪያ መጻህፍት እጥረትን ለማሟላት በትኩረት እየተሰራ ነዉ

የትምህርት ጥራቱን የበለጠ ለማሻሻል የቅድመ አንደኛና የመጀመሪያ ደረጃ የመማሪያ...

የፊንቴክ ሥራ አስኪያጅ በከባድ የማታለል ወንጀል ተከሰሰ

​በአዲስ አበባ የፊንቴክ ኢንቨስትመንት ሥራ አስኪያጅ የሆኑት ዳንኤል ዮሐንስ፣...

ኢራን በሆርሙዝ በኩል ሊያልፉ የነበሩ ሦስት መርከቦችን መመለሷን አሳወቀች

የኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ ዛሬ ጠዋት በሆርሙዝ ወሽመጥ በኩል...