“ድርድሮች ስኬታማ ከሆኑ በዘላቂነት የተለወጠች ኢራንን ታያላችሁ”- ጄዲ ቫንስ

Date:

የአሜሪካ ምክትል ፕሬዝዳንት ጄዲ ቫንስ ከፎክስ ኒውስ ጋር ባደረጉት ቃል ምልልስ “አሜሪካ ከኢራን ጋር በጣም ጥሩ ነጥብ ላይ እንደምትገኝ” ተናገሩ። ከኢራን ጋር የሚደረጉ ድርድሮች ስኬታማ ከሆኑ “የተለወጠች ኢራንን ትመለከታላችሁ” ብለዋል።

“በቅርብ ሳምንታት ውስጥ ኢራናውያን መርከብ ላይ ጥቃት አላደረሱም። በሆርሙዝ ወሽመጥ በኩል ነዳጅ እያለፈ ነው። ምክንያቱም ኢራናውያን መርከብ ላይ ጥቃት ቢፈጽሙ የአጸፋ ምላሽ እንደሚሰጡ ፕሬዝዳንቱ በግልጽ ተናግረዋል” ሲሉም ገልጸዋል።

ቫንስ በቃለ ምልልሳቸው “ከኢራን ጋር የሚደረጉ ድርድሮች ስኬታማ ከሆኑ፣ ስኬታማ እንዲሆኑም እንፈልጋለን፣ በዘላቂነት የተለወጠች ኢራንን የምትመለከቱ ይሆናል” ብለዋል።

“የተለወጠች” ብለው የገለጿት ኢራን ቀጣናዊ ሽብር እና አለመረጋጋት እንደማትደግፍ እንዲሁም በዘላቂነት የኒውክሌር ፍላጎቷን እንደምትሰርዝ ገልጸዋል።

“በዚህም ምክንያት የዓለም ምጣኔ ሃብት ዳግመኛ ይቀበላታል። ይህም ለአሜሪካውያን እና መላው ቀጣና ጥሩ ውጤት ነው” ብለዋል።

ጄዲ ቫንስ አክለውም “የተገባ ባህሪ ካላሳዩ እና ማየት የምንፈልገውን ለውጥ ካላመጡ የኒውክሌር መርሃ ግብራቸው ይወድማል፤ ወታደራዊ አቅማቸው ይንኮታኮታል። አሜሪካ ከእነሱ አንጻር ጠንካራ ናት” ብለው ተናግረዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እግዚአብሔር የሰጠኝን ተልዕኮዎች ፈጽሜያለሁ የአዛዥነት ዘመኔ እያበቃ ነው

የኡጋንዳ የመከላከያ ኃይሎች አዛዥ (CDF) ጄነራል ሙሁዚ ካይኔሩጋባ ከወታደራዊ...

አሐዱ ባንክ 1ነጥብ 07 ቢሊዮን ብር አተረፈ

ባንኩ በተጠናቀቀው የሂሳብ ዓመት ከ3 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር...

በጋምቤላ ከምሽት አንድ ሰዓት በኋላ ነዋሪዎች እንዳይንቀሳቀሱ ተከለከለ

ከጋምቤላ ክልል ዋና ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘው ጋምቤላ...

ፍልውሃ እና ሶደሬ!

ከሐዉለት አህመድ በቀደም ከብዙ ዓመታት በኋላ የፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት ሔጄ...