አሰልጣኝ ገብረመድን ኃይሌ ኢትዮጵያ መድን ከከፍተኛ ሊግ ባደገ በ3ኛው ዓመት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዋንጫን እንዲያነሳም አድርጓል።
ከአሁን በፊት ከጅማ አባ ጅፋር እና መቐለ 70 እንደርታ ጋር የሊጉን ክብር ያሳካው አሰልጣኙ፤ ከ3 የተለያዩ ክለቦች ጋር ዋንጫውን በማንሳት ታሪክ ሰርቷል።
ሀይደር ሸረፋ የዓመቱ ምርጥ ተጫዋች ተብሎ ተመርጧል።
የኢትዮጵያ መድን አምበል ሀይደር ሸረፋ ክለቡ ዋንጫውን እንዲያነሳ ትልቁን አስተዋጽኦም አበርክቷል።
የኢትዮጵያ መድኑ አቡበክር ኑራ የዓመቱ ምርጥ ግብ ጠባቂ ሆኖ ተመርጧል።
የሀዋሳ ከተማው አጥቂ አሊ ሱለይማን በ21 ግቦች ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ሆኖ ሲያጠናቅቅ፤ ባለፈው ዓመትም በተመሳሳይ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ እንደነበር ይታወሳል።
ይታገሱ ታሪኩ የዓመቱ ተስፈኛ ተጫዋች በመሆን ተመርጧል።
በዳኞች ዘርፍ ማኑኤ ወልደጻድቅ ምስጉን ዋና ዳኛ ሆኖ ሲመረጥ፤ መስጠፋ መኪ ምስጉን ረዳት ዳኛ ሆኖ ተመርጧል።
