የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን በ2018 በጀት ዓመት 725.25 ቢሊዮን ብር ገቢ ለመሰብሰብ አቅዶ 738.144 ቢሊዮን ብር መሰብሰቡን አስታውቋል።
ይህም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በ322.4 ቢሊዮን ብር ወይም 77.56 በመቶ ብልጫ ያሳየ ስለመሆኑ ነው የተነገረው።
የበጀት ዓመቱን አፈጻጸም አስመልክቶ ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ (ዶ/ር) ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡ መሆን ኮሚሽኑ በ2019 የበጀት ዓመት ከአንድ ትሪሊዮን ብር በላይ ገቢ ለመሰብሰብ ዕቅድ መያዙም አመላክተዋል።
በተጨማሪም በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 27 ቢሊዮን ብር የገቢ እና 1.9 ቢሊዮን ብር የወጪ በአጠቃላይ 28.9 ቢሊዮን ብር ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎች እንዲሁም የኮንትሮባንድ ዕቃዎችን መያዛቸውን እንስተዋል።
በዚህም 1 ሺህ 835 ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ማዋል እንደተቻለና በአጠቃላይ ኮሚሽኑ በኮንትሮባንድ እና ንግድ ማጭበርበር ሀገር ልታጣ የነበረውን 380.1 ቢሊዮን ብር ማዳኑን አስረድተዋል።
