ጋሽ ይጥና ደምሴ #በሰይፉ_ሾው

Date:

ጋሽ ይጥና ደምሴ #በሰይፉ_ሾው 

እባካችሁ ለጋሽ ይጥና Share ሼር አድርጉት !

ብዙ ደጋጎች ያግዟቸው።

★ ዕድሜዬ 75 ዓመት ነው።

★ በእሱባለው ሙዚቃ በሰራሁት ስራ ሰው

    አድናቆት እያዥጎደጎደልኝ ነው።

★ ዝና ሲመጣ እንዳይገፋንም መጠንቀቅ ነው።

★ ዱላ ከያዝኩኝ 6 ወር ሆነኝ። የነርቭ ችግር ነው።

★ ህክምናው ለውጥ ስለሌለው አቆምኩት።

★ መርካቶ 4ኛ ፖሊስ ጣቢያ አካባቢ ነው የተወለድኩት።

★ 1ኛ ደረጃ የተማርኩት ወሰንሰገድ ት/ቤት ነው።

     2ኛ ደረጃ የተማርኩት አዲስ ከተማ ት/ቤት ነው።

★ ከዚህ በፊት መላክ የተሰኘ ፊልም ላይ ሰርቻለሁ።

     ያልተቀበረው ድራማ ላይ እና መስኮት ላይ ሰርቻለሁ።

★ ቤተሰቦቼን በ1969 ዓ.ም በልጅነቴ ነው ያጣኋቸው።

★ ድሮ ኳስ ተጫዋች ነበርኩኝ። ለአንበሳ አውቶቡስ

     አጥቂ ነበርኩኝ።

★ እስከ 1965 ዓ.ም ድረስ ኳስ ተጫውቻለሁ።

★ በ1969 ዓ.ም ኢህአፓ ስለነበርኩኝ እስር ቤት

    ገብቼ 4 ዓመት ታስሪያለሁ።

★ በወቅቱ ከጎኔ የነበሩት 86 ሰዎች ያለፍርድ

     እየተጠሩ ሞተዋል። ወረቀት ሁሉ ተይዞብኛል።

     ፈጣሪ ዳን ስላለኝ ድኛለሁ።

★ በወቅቱ 1 ብር እየከፈልኩኝ ተደብቄ 1 ወር

    አልቤርጎ ተቀምጫለሁ።

★ በወቅቱ እርስ በእርስ የተበላላንበት የሚያሳዝን

    ጊዜ ነበር።

★ የድሮ ጓጀኛ አይገኝም። ያ ጊዜ ይናፍቀኛል።

★ በጋዜጠኝነት ፦ ድምፅ ጋዜጣ ፣ ጎህ መፅሔት ፣

    ትኩሳት ፣ ረመጥ ጋዜጣ እና ፅናት ላይ ፅፊያለሁ።

★ በጋዜጣ ስራ ላይ ከሪፖርተርነት እስከ 

    ዋና አዘጋጅነት ሰርቻለሁ።

★ አንድ ልጅ አለችኝ። እናቷ ቤተሰቦች ጋር ናት።

    እኔ ብቻዬን ሰሜን ሆቴል አካባቢ ነው የምኖረው።

★ ከ1969 ዓ.ም ጀምሮ ያለውን የመከራ ዘመኔን 

     በመፅሐፍ እፅፋለሁ።

★ ከዚህ በኋላ በሰራተኛ እኖራለሁ እንጂ አላገባም።

★ 2007 ዓ.ም ለስብሰባ ተብሎ የምርጫው ሰሞን

    ናዝሬት ሄጄ 2 ሜትር ጉድጓድ ገብቼ ጥርሶቼን

    አጣሁ። አርቴፊሻሉም በቅርቡ ወለቀ።

★ የዘመን አሻራ ፣ የጥበብ ዋልታዎች የተሰኙ 

     መፅሐፍቶችን ፅፌ አሳትሚያለሁ።

     ማህደረ ጥበባት የተሰኘ መፅሐፍ እያገባደድኩ 

     ነው። የግጥም ስራዎችንም ጨርሻለሁ።

★ ስለአርቲስት ኪሮስ ሀ/ስላሴ አውርቼ አልጠግብም።

     ቶማስ ቶራ ፣ ሰለሞን አስመላሽ ፣ አበበ ተምትም

     ተስፉ ብርሃኔን ጨምሮ በዙሪያዬ 12 የሚደርሱ 

     ወዳጆች አሉኝ።

★ በአሁን ሰዓት ተባራሪ ስራ ከሌለ ገቢ የለኝም።

★ ከኮረና ጊዜ ጀምሮ በጣም ተቸግሪያለሁ።

★  በ100 ብር ሶስት ቀን በልቼ እውላለሁ።

★ ሀገር ፍቅር ቴአትር ቤት ከወዳጆቼ ጋር ቁጭ

    ብዬ ስጫወት ነው የምውለው። ቀን 8 ሰዓት ላይ

    ወደቤት እገባለሁ። ቤት ከገባሁ አልወጣም።

★ መጠጥ ጭራሽ አልጠጣም። ሲጋራ አቁሚያለሁ።

    የታሸገ ውሃ አልጠጣም። የቧንቧ ውሃ ነው

    የምጠጣው።

★ ከ85 ዓመት በላይ እንድቆይ አልፈልግም።

    ሰው ማስቸገርና መደገፍ አልፈልግም።

★ ዘሪሁን ተዝናኑ ስለእኔ ፖስቶ ቫይራል እንዲወጣ

    ስላደረገኝ አመሰግነዋለሁ።

    ( ጋሽ ይጥና 🙏🙏🙏 )

ሰይፉ ፋንታሁን የነርቭ ህክምናቸውን እንዲያገኙ

በዶ/ር ወንድወሰን በኩል አመቻችቶላቸዋል።

የ Smile Speciality Dental Center ባለቤት

ዶ/ር ሰላም ፦

በነፃ የጥርሳቸውን ወጪ ሸፍና ፈገግታቸውን

ልትመልስላቸው ነው።

በተጨማሪም ሰይፉ ሁሌም እንደሚያደርገው

አንድ ወዳጄ ብሎ ነገር ግን ከራሱ ኪስ

100,000.00 መቶ ሺህ ብር ሰጥቷቸዋል።

ክቡራትና ክቡራን ፦ ጋሽ ይጥናን መደገፍ የምትፈልጉ

1000072722578 CBE

24017761 አቢሲኒያ

YETINA DEMISSE 

ይጥና ደምሴ

ስልክ ቁጥር ፦ 0913- 83-83-53

በመደገፍ ተባበሩ ። ለደጋግ ሰዎችም 

Share ሼር በማድረግ አዳርሱ።

የጋሽ ይጥና ደምሴ ምስጋና ፦

እዚህ ቦታ ለተገኛችሁ ተመልካቾች ምስጋናዬን እጀምራለሁ።

አርቲስት ኪሮስ ሀ/ስላሴን ከነባለቤቱ እና ልጆቹ

አመሰግናለሁ። በርበሬና ሽሮ አስፈጭተው የሚደግፉኝ

ናቸው።

እነ ተፈራ ወርቁን በባትሪ ፈልጌ የማላገኛቸው

ውድ ሰዎቼ ናቸው።

ጋዜጠኛ ጋሽ ይጥና ደምሴ ፦ ፈጣሪ ለዘመናት የደከሙበትን

ቆጥሮ የማታ እንጀራ ስለሰጠዎት ደስ ብሎኛል።

የኔን ስም አንስተው ስላመሰገኑኝም ደስ ብሎኛል።

ቀሪው ዕሜዎትን በደስታ እንዲኖሩ እመኝልዎታለሁ።

አክባሪና አድናቂዎት ነኝ።

ዘሪሁን ተዝናኑ

ሞቅ ካለ የሚነበብ ፊርማ ጋር !!!

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከሞዛምቢክ አቻው ጋር ዛሬ ያደረገውን ወሳኝ ጨዋታ 1ለ0 ተሸነፈ !

በ2027 የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የምድብ አራተኛ ጨዋታ የኢትዮጵያ ብሔራዊ...

በአዲስ አበባ ለሶስት ቀናት የሚቆይ የንባብ ፌስቲቫል ሊካሄድ ነው

የንባብ ባህልን ለማነቃቃት ያለመ 15ኛው ከተማ አቀፍ የንባብ ፌስቲቫል...

የጣሊያኗ ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ የኤንሪኮ ማቴይ ሽልማት ተሸለሙ

የጣሊያኗ ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ በአፍሪካና በአውሮፓ መካከል ያለውን...