116ኛው የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ምሥረታ ቀን ተከበረ

Date:



መርሀ ግብሩ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)ን ጨምሮ በርካታ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ነው የተካሄደው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በስነ ስርዓቱ ላይ ባሰሙት ንግግር ” ለተቋም 116 አመታት ማለት ቀላል ትርጉም የሚሰጠው አይደለም ” ብለዋል።

” ቀጣይነት ያለው ሪፎርምና ዘመንን የሚዋጅ አቅም መገንባት አስፈላጊ ነው “ሲሉም ተናግረዋል።

” ባለፉት ጥቂት አመታት በኢትዮጵያ የተቋም ግንባታ በሰላምና ደህንነት ጠባቂ ተቋማት ላይ የተሰራው ስራ አመርቂ ቢሆንም አሁን ዓለም ካለበት ሁኔታ አንጻር በቀጣይነት መሰልጠንና መዘጋጀት ይጠበቅባቸዋል ” ሲሉ ገልጸዋል።

” የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም፣ ሰላምና አንድነት የማረጋገጥ ስራ ከፖሊስ ሰራዊቱ ይጠበቃል ” ብለው ” አንድ መሆን ከቻልን የኢትዮጵያን የግዛት አንድነት እና ብልጽግና ማረጋገጥ እንችላለን ” ሲሉ ተናግረዋል።

” የጠላቶቻችን ፍላጎት እኛን መለየትና መበተን በመሆኑ፥ የእኛ ዓለማ ብሔራዊ ፍላጎቶቻችንን አንጥረን ማወቅ፣ ሰላማችንን መጠበቅ፣ ተባብረን መትጋትና ከወንድም የጎረቤት ህዝቦች ጋር በጋራ መስራት ነው ” ሲሉ ገልጸዋል።

” ከዚያ ያለፈ ነገር ካለ እንደ አባቶቻችን በአርበኝነት ስሜት የኢትዮጵያን አንድነትና ብሔራዊ ጥቅም ማስከበር የሁል ጊዜ ስራችን ነው ” ሲሉ ለሰራዊቱ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

” የኢትዮጵያን ሰላምና አንድነት የማይፈልጉ ሀይሎች በተለመደው መንገድ በክንዳችን ይፈርሳሉ ” ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

#EthiopianFederalPolice#FMC@tikvahethiopia

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በጋምቤላ ከምሽት አንድ ሰዓት በኋላ ነዋሪዎች እንዳይንቀሳቀሱ ተከለከለ

ከጋምቤላ ክልል ዋና ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘው ጋምቤላ...

ፍልውሃ እና ሶደሬ!

ከሐዉለት አህመድ በቀደም ከብዙ ዓመታት በኋላ የፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት ሔጄ...

የተጀመሩ የትምህርት ሪፎርሞችን በጽኑ መሠረት ላይ ለማቆም በቁርጠኝነት መስራት ይገባል

የትምህርት ሚኒስቴር አመራሮችና ሠራተኞች የ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያውን ሩብ...

የአዉሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ የቡና ገበያ መዳረሻዎች እየፈለገ ነዉ

በፈረንጆቹ 2023 የፀደቀው የአውሮፓ ህብረት የደን ጭፍጨፋ ህግ ምርቶች...