20 የኤሌክትሪክ ኃይል ፕሮጀክቶች ከ267 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ በጀት ጠየቁ

Date:

የፌደራል ዋና ኦዲተር 20 የሚሆኑ የኤሌክትሪክ ኃይል ፕሮጀክቶች ከ267 ቢሊዮን ብር በላይ ተጨማሪ በጀት መጠየቃቸዉን እና ከእነዚህም ውስጥ ዘጠኙ ፕሮጀክቶች ከመጀመሪያ በጀታቸው ከ100% እስከ 200% የሚደርስ ጭማሪ ማስመዝገባቸውን አስታውቋል።

በተመሳሳይ የመስኖና የዩኒቨርሲቲ ፕሮጀክቶችም ከመጀመሪያ በጀታቸው ከ78% እስከ 760% የሚደርስ ጭማሪ በማሳየት 17.2 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ ገንዘብ መጠየቃቸው ተገልጿል።

በዋና ኦዲተር በኩል የወጣዉ ሪፖርት እንደሚያመለክተዉ ከ180 በላይ የመንገድ ፕሮጀክቶችም በእቅድ ከተያዘ በጀት 13.2 ቢሊዮን ብር በላይ ተጨማሪ ወጪ ያወጡ ሲሆን፣ ከእነዚህ ውስጥ 75% የሚሆኑት ከቁጥጥር ውጪ የሆነ ወጪ አሳይተዋል።

የአዋጭነት ጥናትና የአፈጻጸም ክፍተቶች
የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ባወጣው የመንግሥት ፕሮጀክት አስተዳደር አዋጅ 1210/2012 መሰረት፣ ፕሮጀክቶች ወደ ትግበራ ከመግባታቸው በፊት ገለልተኛ የአዋጭነት ግምገማ መካሄድ እንዳለባቸው ቢደነግግም፣ በናሙና ከታዩ ፕሮጀክቶች መካከል 52 የመንገድ ፕሮጀክቶች እና 42 የመስኖ ፕሮጀክቶች ያለአዋጭነት ግምገማ ሥራ መጀመራቸው ተረጋግጧል።

CapitalNews

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በአዲስ አበባ የታክስ ዕዳ ምህረት አሰጣጥን የሚያስተዳድር አዲስ ረቂቅ መመሪያ ወጣ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ቢሮ፣ በተለያዩ ከግብር ከፋዮች...

እግዚአብሔር የሰጠኝን ተልዕኮዎች ፈጽሜያለሁ የአዛዥነት ዘመኔ እያበቃ ነው

የኡጋንዳ የመከላከያ ኃይሎች አዛዥ (CDF) ጄነራል ሙሁዚ ካይኔሩጋባ ከወታደራዊ...

አሐዱ ባንክ 1ነጥብ 07 ቢሊዮን ብር አተረፈ

ባንኩ በተጠናቀቀው የሂሳብ ዓመት ከ3 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር...

በጋምቤላ ከምሽት አንድ ሰዓት በኋላ ነዋሪዎች እንዳይንቀሳቀሱ ተከለከለ

ከጋምቤላ ክልል ዋና ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘው ጋምቤላ...