የአዲስ አበባ ፍትሕ ቢሮ በ7 ወራት ከ2 ሺሕ 100 በላይ መዝገቦች ውሳኔ እንደተላለፈባቸው አስታወቀ
በግል አቤቱታ እና በደንብ ጥሰት ክሶች ክርክር ላይ ከነበሩ ከ3 ሺሕ 8 መዝገቦች መካከል፤ 2 ሺሕ 115ቱ የፍርድ ውሳኔ እንደተላለፈባቸው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትሕ ቢሮ አስታውቋል።
የቢሮው ኃላፊ ተክሌ በዛብህ 8 ሺሕ 999 መዝገቦችን የመመርመርና የማጣራት ሥራ መሰራቱን የገለጹ ሲሆን፤ ከ6 ሺሕ በላይ የወንጀል መዝገቦች ደግሞ በእርቅ እደተቋጩ ተናግረዋል።
በተጨማሪም በፍትሐ ብሄር ጉዳዮች ላይ አቅመ ደካማ የሆኑ የሕብረተሰብ ክፍሎች በአቅም ማነስ ምክንያት ሊደርስባቸው የሚችለውን በደል ለማስቀረት ነጻ የሕግ አገልግሎት እንዲያገኙ መደረጉን ተናግረዋል።
ኃላፊው አያይዘውም፤ ቢሮው በትምህርት ቤቶችና በተለያዩ አካባቢዎች የንቃተ-ሕግ ግንዛቤ በማሳደግ በሥነ-ምግባር የታነፀ ዜጋ የመፍጠር ሥራዎችን እየሰሩ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
በቢሮው ባሉት 6 ነፃ የአጭር ቁጥር የስልክ መስመሮች ለሚመጡ የሕግ ምክር አገልግሎት ፈላጊዎች የሕግ-ድጋፍ በመስጠት ላይ እንደሚገኝ የገለጹም ሲሆን፤ በተለይም በሰው መንገድና በሕገ-ወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር ወንጀሎች ላይ በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
አሐዱ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: www.facebook.com/ahah