አቶ አለማየሁ ፋንታ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል

Date:

በባህላዊ የሙዚቃ መሳሪያ ተጫዋጭነታቸው የሚታወቁት ሙዚቀኛው አለማየሁ ፋንታ ስራቸውን የጀመሩት ሃገር ፍቅር ቲያትር ቤት በመቀጠር ነው፤ እዚያም ለ10 ዓመታት ሰርተዋል፡፡

ለ40 ዓመታት ያህል በ ያሬድ የሙዚቃ ትምህርት ቤት በመምህርነት ሲያገለግሉ የቆዩት ሙዚቀኛው፤ በዕድሜአቸው መጨረሻ ጡረታ ከውጡ በኋላ በዚሁ ያሬድ ሙዚቃ ትምህርት ቤት ማገልገላቸውን የሙዚቀኛው የቅርብ ሰው ሆኑት ታዋቂው የበገና መምህር መጋቢ ብሉይ አለሙ አጋ ነግረውናል፡፡

ባህላዊዎቹን የኢትዮጵያ የሙዚቃ መሳሪያዎች በገናን በመደርደር፣ ክራርና መሰንቆን አሳምረው በመጫወት ይታወቁ እንደነበር ከመጋቢ ብሉይ አለሙ አጋ ሰምተናል፡፡

አንጋፋው ሙዚቀኛ አለማየሁ ፋንታ የቀለም ትምህርትን የተማሩ እንዲሁም የድቁና ትምህርትም የነበራቸው ነበሩ፡፡

ሙዚቀኛው ከ6 ወራት በፊት በድንገት ወድቀው እግራቸው በመሰበሩ በህክምና ሲረዱ ቆይተው በትናንትናው እለት መጋቢት 1 ቀን 2017 ዓ.ም ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል፡፡

ስርዓተ ቀብራቸው በነገው ዕለት ፒያሳ በሚገኘው በገነተ ፅጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ከቀኑ በ9 ሰዓት ይፈፀማል።

አንጋፋው ሙዚቀኛ አለማየሁ ፋንታ ባለ ትዳርና 6 ልጆች አባት ነበሩ፡፡

ቀዳሚ ጽሑፍ
ቀጣይ ጥሑፍ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የእግር ኳስ ዳኝነት በኢትዮጵያ

ገነነ መኩሪያ (ሊብሮ) ግዮን መጽሔት :- እግር ኳስ...

ከ989 ሚሊዮን ብር በላይ የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

የጉምሩክ ኮሚሽን ከግንቦት 27 እስከ ሰኔ 3 ቀን 2018...

“እኔ እስካለሁ ድረስ ኢራን የኑክሌር መሣሪያ ባለቤት አትሆንም!”

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ትናንት ሰኔ 5 ቀን...

አገር እንዲህ ዓይንህን ለአፈር ይባላል?

በተጀመረው የአለም ዋንጫ ደቡብ አፍሪካ በሜክሲኮ መሸነፏን ተከትሎ አፍሪካ...