በኢትዮጽያ ባለፉት ሦስት አመታት የሚፈፀሙ ሰብአዊ መብት ጥሰቶች መጨመራቸዉን የኢትዮጽያ ሰብአዊ መብቶች ድርጅት ጥምረት ዳይሬክተር ገለፁ። በኢትዮጽያ የሚፈፀሙ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን በተመለከተ የሰብአዊ መብት ድርጂቶች በየጊዜዉ ሪፖርት የሚያወጡ ቢሆንሞየተጠያቂነት ስርአት ባለመስፈኑ ለችግሮቹ መፍትሄ መስጠት አልተቻለም ተብሏል።
መጠነ ሰፊ የሰብአዊ መብት ጥሰት በአማራ ክልልበግጭት አዉድ ዉስጥየሚፈፀም ሰብአዊ ጥሰት በባለፈዉ ሦስት አመት አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን የሰብአዊ መብት ድርጂቶች ይገልፃሉ ወይዘሮ ዘዉድነሽ በላይና 40የሚደርሱ ሴቶች በጦርነት አዉድ ዉስጥ ጥቃት ተፈፅሞባቸዉ አጥፊዎች ምንም አይነት ሳይፈፀምባቸዉና እነርሱም በይቅርታ ሳይካሱ ዛሬ ላይ መድረሳቸዉ ቁጭት ፈጥሮብናል ይላሉ።
ጦርነት በመጣ ቁጥር ልባችን እእምሮችን ትክክል ሳይሆን ልብሳቸዉን ለብሰዉ በምናይ ሰአት ዉስጣችን እንዴት እንደሚቆስል እንደሚደማ ሁላችንም እንደዛዉ ነን ቢያንስ እንኳን እንደዚህ አይነት ነገር ሲደርስብን መንግስት እርምጃ ወስዶ ለኛ የማሆን ነገር ያዉም የወለደ አለ የተጠቂ ህፃናት ልጃ ገረዶች አሉ አንድ ቤት አምስት ያሳለፍነዉ ህይወት በጣም ይከብዳል ለዚህ እርምጃ ተወስዶ እኛን የሆነ ነገር ላይ ባለማድረሱ በጣም ነዉ የሚሰማን። በኢትዮጽያ የሰብአዊ መብት ድርጂቶች ጥምረት ዳይሬክተር አቶ መስዑድ ገበየሁ ባለፉት ሦስት አመታት የሱብአዊ መብት ጥሰት በኢትዮጽያ በአሳሳቢ ደረጃ እየጨመረ መጥቱል ይላሉ።የሰብዓዊ መብት ጥሰት ሰለባዎችን የሚመለከቱ ሕግጋት
በኢትዮጽያ ዉስጥ ያለዉን የሰብአዊ መብት ሁኔታ ስናይ ከባለፉት ኡምስት አመታት ወዲሆ ብዙየተለወጡ ነገሮች ነበሩ ከተወሰነ ግዜ በኃላ ከዛሬ ሦስት አመታት ወዲህ ግን በሰሜ ኢትዮጽያ የገጠመን ጦርነት ተከትሎ ከዚያም በኃላ በአማራ ክልል ባለዉ በኦሮምያም እንደዚሁ በቤኒሻንጉል ሌሎችም አካባቢዎ በተከታታይነት ማንነትን ትኩረት ያደረጉ ሀይማኖታዊ ፖለቲካዊ ነገሮችን መነሻ ያደረጉ ብዙ አይነት ግጭቶች እየተከሰቱ እነዚህ ነገሮች አጠቃላይ በኢትዮጽያ ዉስጥ ያለዉን የሰብአዊ መብት ሁኔታ ብዚ ችግር ያለበትና አሳሳቢ አድርጎታል።
በኢትዮጽያ የሚፈፀሙ የሱብአዊ መብት ጥሰቶችን በተመሉከተ የሰብአዊ መብት ድርጂቶች በየጊዜዉ ሪፖርት የሚያወጡ ቢሆንም የተጠያቂነት ስርአት ባለመስፈኑ ለችግሮች መፍትሄ ለመስጠት ኡስቸጋሪ ነዉ ሲሉ አቶ መስዑድ ገበየሁ ይናገራሉ።
ክትትል በማድረግ የኛ አይነቶች ሲቪል ሶሻይቲ የኢትዮጵያ ሱብአዊ መብት ኮሚስሽንናሌሎችም እየተከታተሉ ሪፖርት ያደርጋሉ ያም ሆኖ ግን ክትትሎችና ሪፐርቶች መቅረባቸዉ ሳይሆን ዋናዉ ቁም ነገሩ ተጠያቂነት ስርአትን ማምጣት በተለይ ደግሞ በግጭት አዉድ ዉስጥ ለሚኖሩ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች በጣም ሰፊ ስለሚሆኑ በሂደት ዉስጥ የተጠያቂነት ጉዳይ በሚፈለገዉ ደረጃ አለመምጣትን ጨምሮ ችግሮች ስላሉ ለችግሮቹ መፍትሄ በመስጠት በኩል ሁሉም ባለድርሻ አካላት የበኩሉን መወጣት አለበት።አሳሳቢው የሰብአዊ መብት ጥሰት በጋሞ ዞን
የዜጎችን መብት በማክበረርና በማማላት የመንግስት ሚና የላቀ ነዉ የሚሉት ዳይሬክተሩ የኢትዮጵያ መንግስት ቁርጠኝነት ተቋማትን በመገንባት እረገድ ያለዉ ሚና የላቀ ቢሆንም በተግባር ህጎችን በማስፈፀም ረገድ ግን ክፍተት አለ ይላሉ። በተቋማት በኩል የፍትህ ተቋማቶች አሉ ነፃና ገለልተኛ ሁነዉ የሚሰሩ የሰብአዊ መብት ተቋማቶች አሉ አሁን ትልቁ ችግር በአሰራር ደረጃ መሬት ላይ በተግባር ህጎችን በማስፈፀም የመብት ጥሰት መንስኤ የሆኑትን ነገሮችን መፍትሄ በመስጠት እረገድ ነዉ።
አሁን ላይ በኢትዮጵያ ሁሉን ያግባባ የሰብአዊት መብት መከበር እንዲኖር ከዚህ ቀደም የተፈፀሙ የመብት ጥሰቶችን መንግስት እዉቅና ሰጥቶ ለሰብአዊ መብት ጦሰት ምክንያት የሆኑ ግጭቶችን በንግግር ወደ ሰላም መመለስ ያስፈልጋል ሲሉ ይገልፃሉ።
በኢትዮጵያ በባለፍት ጊዚያት በተለያዮ መጠነ ሰፊ የመብት ጥሰት መፈፀማቸዉን መንግስት እዉቅና ሰጥቶ ለዚህ ደግሞ ተጠያቂነትን ማካካሻንዘላቂነት ያለዉ እርቅና ሰላም ማስፍንን ጨምሮ መሰራት ያስፈልጋል።
Date: