3ተኛው ዓለም አቀፍ የኮንስትራክሽን የንግድ ትርዒት ይካሄዳል

Date:

በከተማ እና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር እውቅና ተሰጥቶት በዓለም አቀፉ ዲኤምጂ ኢቨንት (dmg events) የሚዘጋጀው ሦስተኛው ዓለም አቀፍ የቢግ 5 ኮንስትራክት ኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ኤግዚቢሽን፤ ሲምፖዚየም እና የንግድ ትርዒትን ከምስራቅ አፍሪካ መሰረተ ልማት እና የውሀ ኤክስፖ ጋር በመተባበር ከሰኔ 19 እስከ 21 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ በአዲስ አበባ ሚሊኒየም አዳራሽ እንደሚካሄድ ተገልጿል።

የኢትዮጵያን ወደ 67 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት የግንባታ ገበያን እና 395 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት የመሠረተ ልማት ገበያን በመደገፍ ዘርፈ ብዙ ትብብር እና ጠንካራ ስትራቴጂካዊ የንግድ ትሥሥር ይፈጥራል ተብሏል።

የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ፤ ከዚህ ቀደም ሁለት ጊዜ የተካሄዱት የንግድ ትርኢት ከዓለም ሀገራት ጋር ከፍተኛ የሆነ እውቅትና ልምድ ለመቅሰም ያስቻለ እንደነበረ አንስተዋል።

ዘንድሮ በሚካሄደው በሦስተኛው የንግድ ትርኢት ላይ የኮንስትራክሽን ዘርፉን ከማነቃቃት ባሻገር፤ ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ትልቅ አስተዋፅኦ እንዳለው ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ ከግብርና ቀጥሎ ትልቅ የሆነ ኢኮኖሚ የሚንቀሳቀሰው በኮንስትራክሽን ዘርፉ እንደሆነ የገለጹት ሚኒስትሯ፤ ኢትዮጵያ ከዓለም ሀገራት ልምድ ከመቅሰም ባለፈም ያላትን አቅም ለማሳየትና የቴክኖሎጂና የእውቀት ሽግግር ለማድረግ ትልቅ እድል እንደሆነ ተናግረዋል።

የዲኤምጂ ኢቨንት ምክትል ፕሬዝዳንት ቤን ግሪኒሽ በበኩላቸው፤ ቢግ 5 ኮንስትራክሽን የንግድ ትርኢት የኢትዮጵያን የልማት ውይቶች፣ ማበረታቻዎች፣ የኮንፈረንስ እና ኤግዚቢሽኖች ዘርፍን በማዘመን ከፍተኛ ሚና እንዳለው ገልፀዋል።

በኮንስትራክሽንና በመሠረተ ልማት ሥነ-ምኅዳሩ ኢንቨስትመንትን ለመሳብ የሥራ እድል ፈጠራን በመደገፍ እና በንግድ ፍሰቱ ላይ ተጽእኖ በማሳደር ለዘላቂ ልማት አስተዋፅኦ እንደሚያደርግ ተናግረዋል።

ከዚህ ቀደም በነበረው የንግድ ትርኢት በርካታ የሀገር ውስጥ ካምፓኒዎች ከዓለም አቀፍ ካምፓኒዎች ጋር የሥራ ትስስር መፍጠር እንደቻሉ የገለጹት ደግሞ፤ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኢንጂነር ዮናስ አያሌው ናቸው።

በዘንድሮው ዓመትም የሀገር ውስጥ ባለሙያዎች ዓለም የደረሰበት ደረጃ ላይ ለመድረስና ልምድ ለመለዋወጥ ትልቅ እድል እንደሚፈጥርላቸው ተናግረዋል።

ከቻይና፣ ጀርመን፣ ህንድ፣ ጣሊያን፣ ኬንያ፣ ኦማን፣ ሰዑዲ አረቢያ እና የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስን ጨምሮ ከ180 በላይ ከሚሆኑና ከ20 ሀገራት የተውጣጡ ኤግዚቢሽን አቅራቢዎች፣ አዳዲስ የግንባታ እና የመሠረተ ልማት ግብእቶችን በንግድ ትርዒቱ ላይ ያቀርባሉ ተብሏል።

(አሐዱ ሬዲዮ)

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ፈንታዬ በላይነህ የቦስተን ግማሽ ማራቶንን ለሦስተኛ ተከታታይ ጊዜ አሸነፈች

በ2026 የቦስተን ግማሽ ማራቶን ውድድር በሴቶች ምድብ ኢትዮጵያዊቷ አትሌት...

ስፖርቲንግ ሊዝበን ለክርስቲያኖ ሮናልዶ እናት እውቅና ሰጠ

የፖርቹጋሉ ክለብ ስፖርቲንግ ሊዝበን ለክርስቲያኖ ሮናልዶ እናት ማሪያ ዶሎሬስ...

በአዲስ አበባ የታክስ ዕዳ ምህረት አሰጣጥን የሚያስተዳድር አዲስ ረቂቅ መመሪያ ወጣ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ቢሮ፣ በተለያዩ ከግብር ከፋዮች...