3ቱን የባንኩ ሰራተኞች ማን ገደላቸው?

Date:

ከአዲስ አበባ ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ በምትገኘው ሱሉልታ፣ ማንነታቸው ያልታወቁ ታጣቂዎች አርብ ዕለት በፈጸሙት ጥቃት፣ የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ ባልደረቦች የሆኑ ሶስት ሰራተኞች መገደላቸው ታወቀ።

በጥቃቱ፣ ከባንኩ ሰራተኞች በተጨማሪ ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ሌሎች ሰላማዊ ሰዎችም ለህልፈት መዳረጋቸውንና የቆሰሉ ሰዎች መኖራቸውን ከስፍራው የወጡ መረጃዎች አመልክተዋል።

በዚህ አሰቃቂ ጥቃት ህይወታቸው ያለፈው የባንኩ ሰራተኞች፦

◾ አቶ ገመቹ ጥላሁን

◾አቶ ካሳሁን እንኮሳ

◾ አቶ መሳይ አበራ መሆናቸው ታውቋል።

ሱሉልታ ከተማ፣ ለዋና ከተማዋ አዲስ አበባ ባላት ቅርበት ምክንያት ከፍተኛ የጸጥታ ጥበቃ ይደረግላታል ተብሎ ቢታሰብም፣ በተደጋጋሚ የታጣቂዎች ጥቃት ሰለባ ስትሆን ቆይታለች።

እስካሁን ድረስ ለጥቃቱ ኃላፊነቱን የወሰደ አካል የሌለ ሲሆን፣ የጸጥታ ኃይሎችም በጉዳዩ ላይ ይፋዊ መግግለጫ አልሰጡም። ይህ ክስተት፣ በከተማዋ ነዋሪዎች ዘንድ ከፍተኛ ድንጋጤና ስጋትን ፈጥሯል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እግዚአብሔር የሰጠኝን ተልዕኮዎች ፈጽሜያለሁ የአዛዥነት ዘመኔ እያበቃ ነው

የኡጋንዳ የመከላከያ ኃይሎች አዛዥ (CDF) ጄነራል ሙሁዚ ካይኔሩጋባ ከወታደራዊ...

አሐዱ ባንክ 1ነጥብ 07 ቢሊዮን ብር አተረፈ

ባንኩ በተጠናቀቀው የሂሳብ ዓመት ከ3 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር...

በጋምቤላ ከምሽት አንድ ሰዓት በኋላ ነዋሪዎች እንዳይንቀሳቀሱ ተከለከለ

ከጋምቤላ ክልል ዋና ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘው ጋምቤላ...

ፍልውሃ እና ሶደሬ!

ከሐዉለት አህመድ በቀደም ከብዙ ዓመታት በኋላ የፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት ሔጄ...