የኢትዮጵያ 105 ሀገራት ባቀፈው የዓለምአቀፉ አቪዬሽን ድርጅት ቁልፍ የህዝብ መረጃ ልውውጥ ስርዓት አባል መሆኗን የሚያረጋግጥ ሰርተፍኬት ከተቋሙ ዋና መቀመጫ ከሆነችው ካናዳ ተቀብላለች።
የማረጋገጫ ሰርተፍኬቱን የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት የዓለም አቀፉ የሲቪል አቪዬሽን ድርጅት ፕሬዚዳንትና ሌሎች ባለድርሻ አካለት በተገኙበት ተቀብለዋል።
ኢትዮጵያ የዚህ ማዕቀፍ አባል መሆኗ የኢትዮጵያን ፓስፖርት የያዙ ዜጎች በአባልሀገራቱ በሚንቀሳቀሱበት ወቅት ያለምንም እንግልት እንዲጓጓዙ የሚያስችል ነው ተብሏል።
ወደ ኢትዮጵያ በየብስም ሆነ በአየር በተጭበረበረ የጉዞ ሰነድ ለመምጣት የሚሞክሩ አካላትን በቀላሉ ለመለየት የሚረዳና በሀገር ላይ ሊቃጣ የሚችል የደህንነት ስጋትን አስቀድሞ ለመከላከል የሚያግዝ ነው መባሉን የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት መረጃ ያመላክታል።
