አምነስቲ እና ሂዩማን ራይትወች የኤርትራ መንግስትን ኮንነዋል

Date:

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በኤርትራ የተፈጸሙ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን እንዲያጣራ የተቋቋመው የባለሙያዎች ቡድን የስራ ግዜ እንዲያበቃ ለማድረግ የኤርትራ መንግስት ጥረት አያደረገ እንደሚገኝ ተገለጸ።

በሰኔ ወር 2017 ዓ.ም መጀመሪያ ቀናት በሲዊዘርላንድ ጀኔቫ በተካሄደው የመሪዎች ጉባኤ ላይ የኤርትራ የተባበሩት መንግሥታት ልዩ የሰብዓዊ መብት ተከታታይ ራፖርተር ሞሐመድ አብደልሰላም በኤርትራ የሚካሄዱት የሰብአዊ መብተት “ጥሰቶች ስልታዊ ናቸው፤ የተጠያቂነት አስፈላጊነት እጅግ በጣም አጣዳፊ ነው” ሲሉ መግለጻቸው ይታወሳል።

የኤርትራ መንግስት ለመንግስታቱ ድርጅት የሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት ያስገባውን ዶክመንት መመልከቱን ጠቅሶ ሮይተርስ የዜና ወኪል ባሰራጨው ዘገባው ኤርትራ የባለሞያዎቹ ቡድን የስራ ግዜ እንዳይራዘም በመጠየቅ ላይ ትገኛለች።

“የአጣሪ ቡድኑ በኤርትራ ያለው ስራ ገና አልተጠናቀቀም፣ ብዙ ይቀረዋል፤ የምክር ቤቱ አባል ሀገራት የቡድኑን የስራ ግዜ እንዲራዘም ድምጻቸውን ሊሰጡት ይገባል፤ በኤርትራ በመካሄድ ላይ ላሉ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ትኩረት ሊሰጠው ይገባል፤ ከዚህ በፊት ለተፈጸሙ እና አሁንም በመፈጸም ላይ ላሉ ጥሰቶች ተጠያቂ እንዲሆን ማድረግ ይገባዋል” ሲሉ የአምነስቲ የምስራቅና ደቡባዊ አፍሪካ ዋና ዳየሬክተር ቲገረ ቻጉታህ ገልጸዋል።

https://addisstandard.com/Amharic/?p=8236

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አበባው ደሳለው (ዶ/ር) ከማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲና ተሳትፎ ራሳቸውን አገለሉ

የቀድሞው የተወካዮች ምክር ቤት አባልና የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን)...

ኢትዮጵያ በወጣቶች ኦሊምፒክ አራተኛዋን የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች

በሴኔጋል ዋና ከተማ ዳካር እየተካሄደ ባለው አራተኛው የወጣቶች ኦሊምፒክ...

በወራቤ ሆስፒታል የተመረቀው የኦክስጅን ፋብሪካ በሰዓት 60 ኪዩቢክ ሜትር የማምረት አቅም እንዳለው ተገለጸ

በወራቤ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የተመረቀው የኦክስጅን ማምረቻ ፋብሪካ በሰዓት...