የዩክሬኑ ዘለንስኪ ከሩሲያው ፑቲን ጋር ፊት ለፊት ለመወያየት ጥሪ አቀረቡ

Date:

ዘለንስኪ ከፑቲን ጋር በአካል ለመገናኘት ከዚህ በፊትም በተደጋጋሚ ጥሪ ማቅረባቸው የሚታወስ ሲሆን፤ በሁለቱ ሀገራት መካከል ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ ብቸኛው መንገድ ይሄ እንደሆነም ገልጸዋል።

ሞስኮ በጉዳዩ ላይ በሰጠው ምላሽ፤ የሁለቱ ሀገራት ተደራዳሪዎች የጋራ መግባባት ላይ እስካልደረሱ ድረስ የዘለንስኪ የእንገናኝ ጥሪ ዋጋ የለሽ እንደሆነ አስታውቋል።

በሁለቱ ሀገራት መካከል በልዑካን ቡድናቸው የተጀመረው ንግግር እንዲቀጥል የፑቲን ፍላጎት ቢሆንም፤ ዘለንስኪ በበኩላቸው በቱርክ  ከፑቲን ጋር በአካል ተገናኝተው ንግግር እንዲያደርጉ እየወተወቱ ይገኛሉ።

ሁለቱ ወገኖች ከዚህ በፊት ባደረጉት ንግግር እስረኞችን መለዋወጥ ላይ ከስምምነት ቢደርሱም፤ ጦርነቱ ግን መቋጫ አላገኘም።

ኬይቭ ሞስኮ ከዚህ ቀደም ያቀረበችውን የሰላም ሀሳብ አልቀበልም ማለቷም ይታወሳል። 

ዘለንስኪ ትናንት በሰጡት መግለጫ የድርድር ሂደቱ መቀጠል እንዳለበት ጠቅሰው፤ ሌላኛው ዙር ንግግር በሚቀጥለው ሳምንት እንዲቀጥል የሀገራቸው ፍላጎት እንደሆነም ጠቁመዋል።

“የዩክሬኑ ፕሬዚዳንት ከፑቲን ጋር በአካል ለመገናኘት የፈለጉት የፖለቲካ ቅቡልነት ለማግኘት ነው” ሲሉ የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃለ አቃባይ ማሪያ ዛካሮቫ ዘለንስኪን መውቀሳቸውን አርቲ ዘግቧል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

የእግዚአብሔር ሕዝብ ጉባኤ፣ የጌታችንና የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አካልና የመንፈስ...

በመቅደላ ጦርነት ጊዜ የተዘረፉ ቅርሶች ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰዋል

በመቅደላ ጦርነት ጊዜ የተዘረፉ የአጼ ቴዎድሮስ የፀጉር ቁንዳል እና...

ፈረንሳይ የ54 ነጥብ 6 ሚሊዮን ዩሮ ብድር ለመስጠት ተስማምታለች

የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በኢትዮጵያ ጉብኝታቸው ሀገራቸው ለኢትዮጵያ የኃይል...

ትራምፕ ኢራን ላይ ያላቸው ትዕግሥት እየተሟጠጠ መሆኑን ተናገሩ

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከቻይናው መሪ ዢ ጂንፒንግ ጋር...