ሕወሓት፣ የትግራይ ሕዝብ ፍትሃዊ ጥያቄ በጦርነት ዛቻ ሊታፈን አይችልም ሲል ማምሻውን ባወጣው መግለጫ አቋሙን ገልጧል።
ከመሃል አገር ከሄደ የኃይማኖት ልዑካን ቡድን ጋር ሰሞኑን መወያየቱን የገለጠው ሕወሓት፣ የልዑካኑ አባላት በትግራይ ያለው “የሰላም ፍላጎት” እና “ዝግጁነት” ቀደም ሲል ከሠሙት የተለየ መኾኑን ተናግረዋል ብሏል።
ሕወሓት፣ በትግራይ በኩል ለግጭት የሚጋብዝ እንቅስቃሴ በሌለበት ኹኔታ ፌደራል መንግሥቱ የማስፈራራት ዘመቻ እያካሄደ፣ የታጠቁ ሃይሎችን እያደራጀና እያስታጠቀ ይገኛል በማለትም መክሰሱን ዋዜማ ዘግባለች፡፡
መንግሥት በግጭት ማቆም ስምምነቱ መሠረት ግዴታውን እስካልተወጣ ድረስ፣ የትግራይ ሕዝብ ከመሪ ድርጅቱ ጋር ለኅልውናውና ሉዓላዊነቱ ሠላማዊ የፖለቲካ ትግሉን ይቀጥላል ሲል ሕወሓት አቋሙን ገልጧል።
