የሳንባ ካንሰርን ሳይባባስ እና ሳይሰራጭ በምርመራ መለየት ይቻላል

Date:

የዐለም የሳንባ ካንሰር ቀን በዐለም ለ14ኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ2ኛ ጊዜ “የሳንባ ካንሰርን ሳይባባስ እና ሳይሰራጭ በምርመራ መለየት ይቻላል!” በሚል መሪ ቃል የኢትዮጵያ ቶራሲክ ሶሳይቲ ከጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ጋር በመተባበር በተለያዩ መርሀግብሮች ከሀምሌ 21 እስከ 25 ሰፊ የግንዛቤ ማስጨበጫ እና ነፃ የቅድመ ልየታ ምርመራ እየሰጠ ይገኛል።

ይህ ዓለም ዐቀፍ ቀን በብሪስቶል ማየርስ ስኩዊብ ፋውንዴሽን (BMSF) ድጋፍ ኢትዮጵያ ላይ የሚተገበረው  የሳንባ ካንሰር ፕሮጀክት አካል ነው።

የሳንባ ካንሰር በዓለም ዐቀፍ ደረጃ በስፋት ከሚታወቁት የካንሰር አይነቶች አንዱ ሲሆን በካንሰር ምክንያት ለሚከሰት የሞት ምጣኔ ደግሞ በቀዳሚነት ይቀመጣል፡፡

የሳንባ ካንሰር ህክምና ውጤታማነት ካንሰሩ በታወቀበት ጊዜ ካለው የስርጭት ደረጃ ጋር በቅርበት የተቆራኘ ነው፡፡ ይህም ማለት በሽታው በእንጭጭነቱ ወይም ሳይዛመት በፊት መለየት ከተቻለ የታካሚውን የህክምና ውጤት በእጅጉ ማሻሽል ይቻላል፡፡

በኢትዮጵያ ከ80% የሚልቁት የሳንባ ካንሰር ተጠቂዎች በጣም ዘግይተው ወደ ህክምና ተቋማት እንደሚመጡ ጥናቶች ያሳያሉ። ይህም የሳንባ ካንሰር ምልክቶች ግንዛቤ አነስተኛ መሆኑን እና የቅድመ ምርመራ እና ክትትል ትግበራ አንደሀገር ያልዳበረ መሆኑ እንደ ምክንያት ሊጠቀስ ይችላል።

በኢትዮጵያ የሳንባ ካንሰር ምጣኔ እየጨመረ መምጣቱን አመላካች ጥናቶች መኖሩን ታሳቢ በማድረግ፤ የሳንባ ካንሰር ቅድመ ምርመራ እና የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን አጠናክሮ መቀጠል እንደሚያስፈልግ ያመላክታል።

➡️ ሲጋራ እና ሺሻ ማጨስ፣ 
➡️ ለከባድ ጭስ እና ጥቀርሻ ያለ ተጋላጭነት፣
➡️ በስራ ቦታ ለመርዛማ ብናኞች/ ንጥረ ነገሮች ያለ ተጋላጭነት እና ስር የሰደደ የመተንፈሻ አካላት በሽታ ታማሚ መሆን በጥናት የተለዩ አጋላጭ መንስኤዎች በመሆናቸው ቅድመ ምርመራ እና የህክምና ክትትል ማድረግ፤ የባህሪ ለውጥ ማድረግ በሽታውን በመከላከል አና በመግታት ሂደት ውስጥ ጉልህ ሚና አለው፡፡

ለተጨማሪ መረጃ የኢትዮጵያ ቶራሲክ ሶሳይቲን ድህረ ገጽ ይመልከቱ
https://ethiopianthoracicsociety.org/ets-lung-cancer-screening/

ሁሉም ባለድርሻ አካላት እና የሚዲያ ተቋማት በሳንባ ካንሰር ላይ ግንዛቤ በመፍጠር ሂደት ውስጥ ሚናቸውን በመጫወት  ይህንን ወሳኝ ዘመቻ እንዲቀላቀሉ የኢትዮጵያ ቶራሲክ ሶሳይቲ ጥሪ ያቀርባል፡፡

በተቀናጀ ጥረት ህይወትን የማዳን እና ለሁሉም ኢትዮጵያውያን ጤናማ የወደፊት ዕድል በመፍጠር ትልቅ ተፅእኖ መፍጠር እንችላለን።

የኢትዮጵያ ቶራሲክ ሶሳይቲ የሚሰራቸውን ስራዎች እና ወቅታዊ እና ሳይንሳዊ መረጃዎችን በመተንፈሻ አካላት እና ፅኑ ህሙማን ህክምና ላይ ለማግኘት ከታች ባሉት ማህበራዊ ሚድያዎች ትስስር ይፍጠሩ

የኢትዮጵያ ቶራሲክ ሶሳይቲ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ጥቃት አድራሹ ከካሊፎርኒያ መሆኑን ትራፕ ገለፁ

ትናንት ቅዳሜ ምሽት በዋይት ሃውስ የጋዜጠኞች ማኅበር የእራት ግብዣ...

በኬንያ የመንገደኞች አውሮፕላን ከመስመሩ ወጥቶ ተከሰከሰ

ዛሬ ረፋድ ላይ በኬንያ ማንዴራ የአውሮፕላን ማረፊያ አንድ...

አቶ ጀማል አህመድ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ተጨማሪ 26 ሚሊየን ብር ሰጡ

አቶ ጀማል አህመድ ባሳለፍነው ወር ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ  ከሰጠው...

“የቻይና-አፍሪካ የምርምር ማዕከል”በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሊከፈት ነው

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከቻይና-አፍሪካ ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር "የቻይና-አፍሪካ የምርምር...