50 ሺህ ብር የሚያሸልመው ሀገር አቀፍ የሂሳብ ትምህርት የመጨረሻ ውድድር ይካሄዳል

Date:

የሂሳብ ትምህርት ውድድሩ ከሁሉም ክልሎች እና የከተማ አስተዳደሮች የተውጣጡ ተማሪዎቾ የሚሳተፉበት ሲሆን ውድድሩን ያሸነፉ 50 ሺህ ብር ይሸለማሉ ተብሏል።

ሁለተኛና ሶስተኛ ለወጡ ደግሞ 45 ሺህ እና 40 ሺህ ብር ያገኛሉ ነው የተባለው።

በዚህ ውድድር ከ3ኛ ክፍል እስከ 12ኛ ክፍል ያሉ 6 ሺህ ተማሪዎች እንደሚሳተፉበት ተነግሯል።

ከ3ኛ እስከ 8ኛ ክፍል ያሉት በሀገሪቱ ባሉ 23 የአፍ መፍቻ ቋንቋዎቾ ፈተናውን የሚወስዱ ሲሆን ከ9 እስከ 12ኛ ክፍል ያሉት ደግሞ በእንግሊዘኛ ይፈተናሉ ተብሏል።

ከገንዘብ ሽልማት ባለፈ የሰርተፊኬት እና የዋንጫ ሽልማት ይኖረዋል ተብሏል።

በውድድሩ በአጠቃላይ ከ2 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር በላይ የጥሬ ገንዘብ ለሽልማት የወጣ ሲሆን ይህም እንደሀገር ከናይጄሪያ እና ደቡብ አፍሪካ ቀጥሎ ከፍተኛ መሆኑ ተጠቁሟል።

ከ80 ከተሞች የተውጣጡ ተማሪዎች በየከተማው ከየካቲት ወር ጀምሮ የዙር ውድድር አድርገው ከፍተኛ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች ሐምሌ 30 ቀን አዲስ አበባ የሚገቡ ሲሆን በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እና በ4 ኪሎ ካምፓስ ያርፋሉ ተብሏል።

ውድድሩ ከነሐሴ 1 እስከ ነሐሴ 3 ቀን 2017 ዓ.ም የሚደረግ ሲሆን መዝጊያቅ በሚሊኒየም አዳራሽ ይከናወናል ተብሏል።

(አራዳ ኤፍ ኤም)

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከ989 ሚሊዮን ብር በላይ የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

የጉምሩክ ኮሚሽን ከግንቦት 27 እስከ ሰኔ 3 ቀን 2018...

“እኔ እስካለሁ ድረስ ኢራን የኑክሌር መሣሪያ ባለቤት አትሆንም!”

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ትናንት ሰኔ 5 ቀን...

አገር እንዲህ ዓይንህን ለአፈር ይባላል?

በተጀመረው የአለም ዋንጫ ደቡብ አፍሪካ በሜክሲኮ መሸነፏን ተከትሎ አፍሪካ...

አሜሪካ እና ኢራን የመጀመሪያ ደረጃ ስምምነት በ24 ሰዓት ውስጥ እንደሚፈራረሙ ፓኪስታን አስታወቀች

ዩናይትድ ስቴትስ እና ኢራን በሰላም ድርድሩ ማዕቀፎች ላይ መስማማታቸውን...