አዲስ አበባ የዓለማችን ከፍተኛ የአየር ብክለት ካለባቸው ከተሞች አንዷ ናት

Date:

በዓለም የአየር ጥራት መረጃ ድርጅት (IQAir) የወጣ ዘገባ መሰረት፣ የኢትዮጵያ ዋና ከተማ አዲስ አበባ የአየር ጥራት መጠን አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን አስታወቀ።

ሪፖርቱ እንደሚያሳየው፣ ከተማዋ የሐምሌ 30 ቀን 2017 ዓ.ም. በዓለም አቀፍ ደረጃ ከሚገኙ ከፍተኛ የአየር ብክለት ካለባቸው ከተሞች መካከል በአራተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች።

በዚሁ ቀን በተደረገው ምዘና፣ የአዲስ አበባ የአየር ጥራት መረጃ ጠቋሚ (AQI) 147 ላይ የደረሰ ሲሆን፣ ይህም ደረጃ በተለይ እንደ የመተንፈሻ አካላት ወይም የልብ ህመም ላለባቸው የህብረተሰብ ክፍሎች “ለጤና ተጋላጭ ያልሆነ” ተብሎ ተመድቧል።

በአየር ውስጥ የሚገኘው ጥቃቅን ብናኝ (PM2.5) መጠን በኪዩቢክ ሜትር 54.2 ማይክሮ ግራም መድረሱ የዓለም ጤና ድርጅት የ24 ሰዓት የ15 ማይክሮ ግራም ገደብን በከፍተኛ ደረጃ አልፏል።

የአዲስ አበባን የአየር ብክለት የሚያባብሱት ምክንያቶች የተሽከርካሪ ጭስ ፣ የባዮማስ ማቃጠል፣ አቧራ ( የግንባታ ስራዎች፣ አስፋልት ያልተነጠፉ መንገዶች እና የአሸዋ ማውጫ ቦታዎች) ብክለቱን ይጨምራሉ።

እንዲሁም ቆሻሻ ማቃጠል፣ እና እንደ ሲሚንቶ ፋብሪካዎችና አነስተኛ ኢንዱስትሪዎች የሚያመነጩት ጭስ ለብክለቱ ተጨማሪ አስተዋጽኦ እንደሚያርጉ ካፒታል ተመልክቷል።

የኢትዮጵያ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን የአየር ብክለትን ለመቀነስ የሚያስችል አገራዊ ዘመቻ ቢጀምርም፣ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል የጋራ ትኩረትና ትብብር ለችግሩ ዘላቂ መፍትሄ ወሳኝ መሆኑ ታውቋል።

CapitalNews

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አበባው ደሳለው (ዶ/ር) ከማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲና ተሳትፎ ራሳቸውን አገለሉ

የቀድሞው የተወካዮች ምክር ቤት አባልና የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን)...

ኢትዮጵያ በወጣቶች ኦሊምፒክ አራተኛዋን የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች

በሴኔጋል ዋና ከተማ ዳካር እየተካሄደ ባለው አራተኛው የወጣቶች ኦሊምፒክ...

በወራቤ ሆስፒታል የተመረቀው የኦክስጅን ፋብሪካ በሰዓት 60 ኪዩቢክ ሜትር የማምረት አቅም እንዳለው ተገለጸ

በወራቤ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የተመረቀው የኦክስጅን ማምረቻ ፋብሪካ በሰዓት...