የትራምፕና ዘለንስኪ ውይይት

Date:


የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮለድሚር ዘለንስኪ ከአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር ሊወያዩ መሆኑ ተሰምቷል። ዘለንስኪ ለዚሁ ውይይት ወደ በርሊን ያቀናሉ የተባለ ሲሆን ከትራምፕ ጋር ሰፋ ያለ የቪዲዮ ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ትራምፕ ከዘለንስኪ ባሻገር ሌሎች የአውሮፓ ሀገራት መሪዎች ጋር በኦንላይን ውይይት ያደርጋሉም ተብሏል።

ውይይቱ በዋነኝነት ትራምፕ በመጪው አርብ ከሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር ሲገናኙ የዩክሬንን ፍላጎት ያማከለ ስምምነት እንዲያደርጉ ለመምከር መሆኑም ተሰምቷል።

የጀርመኑ ቻንስለር ፍሬድሪክ ሜርዝ ለዚሁ የቪድዮ ስብሰባ ዘለንስኪን ጨምሮ እንግሊዝ ፤ፈረንሳይ፤ የአውሮፓ ህብረት አመራሮችን ወደ በርሊን ጠርተዋልም ተብሏል።

ትራምፕ ፑቲንን በመጪው አርብ በአላስካ ከማግኘታቸው አስቀድሞ የሚደረገው ይህ የቪድ ስብሰባ ላይ የትርምፕ ምክትል ጄዲ ቫንስ ተሳታፊ ይናሉ ተብሏል።

የመጪው አርብ የዶናልድ ትራምፕና የፑቲን በአካል መገናኘት የሩሲያ ዩክሬን ጦርነት ከተጀመረ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜም ያርገዋል።በዚህም ኬቭ ከፍተኛ ስጋት ውስጥ መግባቷ ተሰምቷል።

ዘገባው የፍራንስ 24 ነው።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...