በሊቢያ ቤንጋዚ በተካሄደው የታዳጊ ወጣቶች ዓለም አቀፍ የብስክሌት ውድድር የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በበላይነት አጠናቅቋል።
ብሄራዊ ቡድኑ ውድድሩ ላይ በቡድን እና በግል የተሳተፈ ሲሆን በሁለቱም ምድቦች በአንደኝነት አጠናቅቋል።
በቡድን በተደረገው ውድድር ኢትዮጵያ፣ ሞሮኮ እና ግብፅ በተከታታይ ከአንድ እስከ ሶስት ያለውን ደረጃ ሲይዙ፣ በግል በተደረገው ውድድር ደግሞ ኢትዮጵያ በአንደኝነት እና በሶስተኝነት ስትጨርስ፣ ሞሮኮ ሁለተኛ በመሆን ውድድራቸውን ማጠናቀቃቸውን ብሄራዊ ቡድኑ ለኤ ኤም ኤን በላከው መረጃ ገልጿል ።
ውጤቱን መሰረት በማድረግም የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የተዘጋጁትን ሁለቱንም የወርቅ ሽልማቶች እና የገንዘብ ማበረታቻ መውሰድ ችሏል።
