የአሸንዳ፣ አሸንድዬ እና ሶለል በዓላት ዝግጅት መጠናቀቁ ተገለጸ

Date:

‎በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል በየዓመቱ ከነሐሴ ወር አጋማሽ ጀምሮ ለሚከበሩት አሸንዳ፣ አሸንድዬ እና ሶለል በዓላት የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች መጠናቀቃቸውን የአማራ እና የትግራይ ክልል ባህል እና ቱሪዝም ቢሮዎች አስታውቀዋል፡፡ 

ነጻነት እና ሰላምን የሚሰብከው፤ ሴቶች በዘፈን እና በጭፈራ የሚያከብሯቸው በዓላት ለብዙ ሺሕ ዓመታት በአካባቢዎቹ ሲከበሩ መቆየታቸውን ስለበዓላቱ የተጸፉ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡

በዚህም በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ሻደይ፣ አሸንድዬ፣ ሶለልና እንግጫ ነቀላ በዓላት እንደየአካባቢው ወግና ልማድ በተለያዩ ባህላዊ አልባሳት እና ጌጣጌጦች አምረውና ደምቀው አደባባይ በሚወጡ ልጃገረዶች ባህላዊ ዜማዎች እና ውዝዋዜዎችን ታጅበው በድምቀት ይከበራሉ።

በተመሳሳይ በትግራይ ክልልም የአሸንዳ በዓል በልጃገረዶች ልዩ የጸጉር አሰራር፣ የተለየ አለባበስ፣ ህብረ ዝማሬ እና የተለየ የአጊያጊያጥ ስርዓት ደምቆ በተለይም በመቀለ ከተማ በልዩ ሁኔታ በድምቀት ይከበራል፡፡

በተለይ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የአክባሪዎቻቸው ቁጥር እየጨመረ እና የቱሪዝም መስህብ እየሆኑ የሚገኙትን እነዚህን በዓላት፣ ባህላዊ ትውፊትን በጠበቀ መልኩ ለማክበር እና ለማስከበር ጥረት እየተደረገ እንደሚገኝ የክልሎቹ ባህል እና ቱሪዝም ቢሮዎች ገልጸዋል

ለክብረ በዓሉ የሚመጡ እንግዶችን ምቾት እና ማረፊያ ለመጠበቅ ዝግጅት መደረጉንም ጨምረው አስታውቀዋል፡፡

የአማራ ክልል ባህል እና ቱሪዝም ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ዓባይ መንግስቴ፤ “አሸንድዬ፣ ሻደይ እና ሶለል በተለየ ድምቀት ከሚከበሩባቸው የክልሉ አካባቢዎች መካከል ጎንደር፣ ሰሜን ወሎ እና ዋግህምራ ይጠቀሳሉ” ብለዋል።

አቶ ዓባይ የክብረ በዓሉን ሁኔታ አስመልክቶ ለአሐዱ እንደተናገሩት፤ በዓሉ ያለምንም የፀጥታ ችግር ተከብሮ እንዲያልፍ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች በስፋት ተሰርተዋል፡፡

የትግራይ ክልል የባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ዶክተር አፅብዓ ገብረእግዚአብሔር በበኩላቸው፤ በዓሉን ለመታደም ወደ ክልሉ የሚመጡ ኢትዮጵያዊንን እና የውጭ ዜጎችን በሰላም ተቀብሎ ለመሸኘት የፀጥታን ጨምሮ በሁሉም ረገድ የሚደረጉ ዝግጅቶች መጠናቀቃቸውን ተናግረዋል፡፡  

ሻደይ፣ አሸንዳ፣ አሸንድዬ እና ሶለል በሁለቱ ክልሎች ለሦስት ተከታታይ ቀናት የሚከበሩና በአብዛኘው ሴቶች እና ልጃገረዶች የሚሳተፉባቸው ዓመታዊ ክብረ በዓላት ሲሆኑ፤ ነጻነት እና ሰላምን ከመስበካቸው በተጨማሪ የክረምቱን ወቅት ማብቃትና የወንዙን መጉደል እና የጸሐይን መውጣት ያበስራሉ፡፡

(አሐዱ ሬዲዮ)

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በጋምቤላ ከምሽት አንድ ሰዓት በኋላ ነዋሪዎች እንዳይንቀሳቀሱ ተከለከለ

ከጋምቤላ ክልል ዋና ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘው ጋምቤላ...

ፍልውሃ እና ሶደሬ!

ከሐዉለት አህመድ በቀደም ከብዙ ዓመታት በኋላ የፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት ሔጄ...

የተጀመሩ የትምህርት ሪፎርሞችን በጽኑ መሠረት ላይ ለማቆም በቁርጠኝነት መስራት ይገባል

የትምህርት ሚኒስቴር አመራሮችና ሠራተኞች የ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያውን ሩብ...

የአዉሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ የቡና ገበያ መዳረሻዎች እየፈለገ ነዉ

በፈረንጆቹ 2023 የፀደቀው የአውሮፓ ህብረት የደን ጭፍጨፋ ህግ ምርቶች...