በዋሽንግተን ያለው የሱዳን ኤምባሲ ቮጎል የተሰኘ ቡድን ሲቀጥር ለድርጅቱ በወር 40,000 ዶላር ይከፍላል ተብሏል።
ቡድኑ ከአሜሪካ ባለስልጣናት ጋር በመገናኘት ስለ ሰብዓዊ ሁኔታና የውጪ ግንኙነት ፖሊሲ ንግግር በማድረግ የማግባባት ስራ ይሰራል።
ሱዳን ለተቋሙ በወር ከምትከፍለው 40,000 ዶላር በተጨማሪ የትራንስፖርት ወጪንም ትሸፍናለች ሲባል ኮንትራታቸው ባለፈው ሰኔ ወር መፈረሙን እና እስከ አመቱ መጨረሻ ማለትም እስከ መጪው ታህሳስ ወር ድረስ እንደሚቆይ ተሰምቷል።
በርከት ያሉ የአፍሪካ ሃገራት የአሜሪካ ከፍተኛ ባለስልጣናትን ለማግባባት የአግባቢ ቡድኖችን መቅጠራቸው የተለመደ ሲሆን ለቡድኖቹም ረብጣ ዶላሮችን እንደሚያወጡ በተደጋጋሚ መዘገቡ ይታወሳል።
Source: Sudan Tribune
