ቶም ክሩዝ፣ ከዶናልድ ትራምፕ የቀረበለትን የኬኔዲ የክብር ሽልማት ውድቅ አደረገ

Date:

የሆሊዉድ ኮከብ ተዋናይ ቶም ክሩዝ በፕሬዝደንት ትራምፕ የቀረበለትን የ2025ቱ የኬኔዲ የክብር ሽልማት ስነስርዓት ላይ እንደማይገኝ አስታውቋል።

ቶም ክሩዝ፣ እኤአ ታህሳስ 7 ቀን 2025 በዶናልድ ትራምፕ አዘጋጅነት የሚካሄደው የኬኔዲ የክብር ሽልማት ላይ በፊልም ቀረፃ ምክንያት በስነስርዓቱ ላይ እንደማይገኝ ይፍ አድርጓል። ቶም ክሩዝ በፊልም ስራ ስለተጠመደ የ2025ቱ የኬኔዲ ሴንተር የክብር ሽልማት ግብዣን ውድቅ ማድረጉን ተከትሎ ዶናልድ ትራምፕን ያበሳጨ ድርጊት ሆኗል።

ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የ2025 የኬኔዲ የክብር ተሸላሚዎችን በግላቸው የመረጡ ሲሆን ከቶም ክሩዝ በተጨማሪ እንደ ሲልቨስተር ስታሎን፣ የሃገረሰብ ሙዚቃ አቀንቃኙ ጆርጅ ስትሬት፣ የዲስኮ ሙዚቃ አቀንቃኟ ግሎሪያ ጋይኖር እና ሮክ ባንድ ኪስ የመሳሰሉ ኮከቦችን ያካትታል።

የኬኔዲ የክብር ሽልማት በሀገሪቱ ካሉት እጅግ የተከበረ የጥበብ ስኬት ክብረ በዓላት አንዱ ሲሆን ታህሳስ 7 ቀን ይካሄዳል። ነገር ግን ከትራምፕ እጅ የኬኔዲ የክብር ሽልማትን ለመቀበል አንዱ ሆኖ የተመረጠው የሆሊውድ ኮከብ ተዋናይ ቶም ክሩዝ ግብዣውን አልተቀበለውም።

የኬኔዲ የክብር ሽልማት በፊልም፣ በሙዚቃ፣ በትያትር  እና ዳንስ እንዲሁም በአሜሪካ ባህል ላይ ጉልህ ሚና ለነበራቸው ሰዎች የሚበረከት የእውቅና ሽልማት ነው።

የኬኔዲ የክብር ሽልማት ታህሳስ 7 ቀን 2025 በዋሽንግተን ከተማ የሚካሄድ ሲሆን በ CBS ቴሌቭዥን የቀጥታ ስርጭት ሽፋን ያገኛል።

የኬኔዲ ሽልማት ስነስርዓት እኤአ በ1978 የጀመረ ሲሆን፣ በየዓመቱም ታህሳስ 7 ለ5 ግለሰቦች እውቅና ይሰጣል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አበባው ደሳለው (ዶ/ር) ከማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲና ተሳትፎ ራሳቸውን አገለሉ

የቀድሞው የተወካዮች ምክር ቤት አባልና የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን)...

ኢትዮጵያ በወጣቶች ኦሊምፒክ አራተኛዋን የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች

በሴኔጋል ዋና ከተማ ዳካር እየተካሄደ ባለው አራተኛው የወጣቶች ኦሊምፒክ...

በወራቤ ሆስፒታል የተመረቀው የኦክስጅን ፋብሪካ በሰዓት 60 ኪዩቢክ ሜትር የማምረት አቅም እንዳለው ተገለጸ

በወራቤ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የተመረቀው የኦክስጅን ማምረቻ ፋብሪካ በሰዓት...