መኮንን ላዕከን ዳግም ተዳረ -ከዩቶፒያ ቴክኖሎጂ መኪና ተሸለመ

Date:

ነሐሴ 22 ቀን 2017 ዓ.ም በዝምታ ሬስቶራንትና ላውንጅ ልዩ ምሽት አለፈ። አርቲስት መኮንን ላዕከ የ57ኛ ዓመት ልደቱ በልዩ ዝግጅት ተከበረ።

የመኮንን የአመታት ህልምና ፍላጎትም ተፈጽሞ ዳግም ከ ካለቤቱ ተሞሸረ። አራት ልጆቹም አጃቢና ሚዜዎቹ ሆኑ።

ነገሩ እንዲህ ነው!!!

አርቲስት መኮንን ላዕከ በህይወቱ ውስጥ ከሚቆጩት ነገሮች አንዱ ባለቤቱን ወይዘሮ ሰላማዊትን በቬሎ አለማግባቱ ነው። ይህ ቁጭት የመኮንን ብቻም ሳይሆን የባለቤቱም ጭምር መሆኑን የቅርብ ሰዎች ይመሰክራሉ።

እናም ይህንን ምኞት ለማሳካት እና መኮንን ላዕከን ለማስደሰት ያለመ ኮሚቴ በራስ ተነሳሽነት ተቋቋመ። ኮሚቴው ስለ ዝግጅቱ፣ስለዝግጅቱ ማከናወኛ ስፍራ፣ስለዝግጅቱ ይዘት፣ስለሚጠሩ እንግዶች፣ስለ ዝግጅቱ ምስጢራዊነት፣መኮንን ላዕከ በዕለቱ ሊደረግለት ስለሚገቡ ድንገቴ ስጦታዎች…… ወዘተ ለአንድ ወር መከረ።ለፋ።

በመጨረሻም ትናንት ልፋቱ እውን ሆነ። ስለ ልደቱም ሆነ ስለ ዳግም መሞሸሩ መኮንን እና ባለቤቱ እንዳያውቁ ከባድ ምስጢርን የመጠበቅ ስራ ተከናወነ። መኮንንም ባለቤቱም ባልጠበቁት ዕለት ልደትና ሰርጋቸውን አደረጉ።

መቼም ምሽቱ ልዩ ነበር።መኮንና ባለቤቱ የነበራቸው መደንገጥና ያለማመን ሁሉም እንግዶች ላይ ተጋብቷል። ህልሙን እውን እናድርግ ብሎ የቆረጠው ኮሚቴም በአንድ ወር ቆይታው ብዙ ስለለፋ ሁሉም ተሳካ። በድንገቴ ላይ ድንገቴው ቀጠለ። ለመኮንን መኪና ማግኘት ህልሙ የነበረው ኮሚቴ ህልሙ ተሳክቶ መኮንን የመኪና ባለቤት መሆን የሚችልበትን ዕድል ፈጠረ። በዲጄ ቤቢ (አዲስ ሚዩዚክ) ትልቅ ጥረት ታግዞ ዩቶፒያ ቴክኖሎጂ ደግሞ መኪና ለመስጠት ቃል ገባ። ትናንት ምሽት በዝምታ ሬስቶራንትና ላውንጅ የዩቶፒያ ቴክኖሎጂ ማኔጂንግ ዳይሬክተር አቶ አዶኒክ ወርቁ እና የድርጅቱ አምባሳደር አርቲስት እንግዳሰው ሀብቴ በዝግጅቱ ላይ ተገኝተው የመኪናው ስጦታ እውንነትን አረጋገጡ።

ቴምር ሪል ስቴት 300,000 ብር ለመኮንን ልደት ስጦታ ላከ። የማስታወቂያ ባለሙያው እና የረዥም ዓመታት ወዳጁ ዘላለም ኩራባቸው የ1,000 ሚሊዮን ብር ስጦታ ላከ። ጎልደን ዲዛይን ምርጥ እና በልዩ ሁኔታ የተሰራ የሀገር ባህል ልብስ ለጥንዶቹ አበረከተ። የስዕል እና ሌሎች ስጦታዎችም ቀጠሉ።

አድዋ ባንድ የመኮንን ላዕከን ልደትና ዳግም ሰርግ አደመቀ። ስንግ ኬተሪንግ እንግዶቹን ጭምር ጋበዘ።focus studio ይህንን ውብ ዝግጅት ሰናጅ ሆነ። ድምጻዊት ሳሮን (ሚሶ ነገያ) ሜከአፑ ላይ ተጠበበችበት

ማን ያልተባበረ አለ????ማንም።

ስሜትን ለመግለጥ የሚያስቸግረ ምሽት ሆነ። ላዕከ እና ባለቤቱ ኮሚቴውን በከፍተኛ መገረም ውስጥ ሆነው አመሰገኑ እንግዶች ፍቅራቸውን አፈሰሱት። ደስታቸውንም ተጋሩ።
ድንቅ ምሽት!!!!
የሰው ፍቅር ሞልቶ የፈሰሰበት ዝግጅት!!!!

ምርጥ የኮሚቴ ስብስብ። ምርጥ ትብብር። ምርጥ ርብርብ። የማይረሳ ዝግጅት ።

መኮንን ላዕከ በድጋሚ መልካም ልደት።
እንኳንም ህልምህን ኖርከው!!!!

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አበባው ደሳለው (ዶ/ር) ከማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲና ተሳትፎ ራሳቸውን አገለሉ

የቀድሞው የተወካዮች ምክር ቤት አባልና የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን)...

ኢትዮጵያ በወጣቶች ኦሊምፒክ አራተኛዋን የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች

በሴኔጋል ዋና ከተማ ዳካር እየተካሄደ ባለው አራተኛው የወጣቶች ኦሊምፒክ...

በወራቤ ሆስፒታል የተመረቀው የኦክስጅን ፋብሪካ በሰዓት 60 ኪዩቢክ ሜትር የማምረት አቅም እንዳለው ተገለጸ

በወራቤ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የተመረቀው የኦክስጅን ማምረቻ ፋብሪካ በሰዓት...