ኢትዮጵያ እና ደቡብ ሱዳን የአየር መንገድ ስትራቴጂካዊ አጋርነት ውይይታቸውን አደሱ

Date:

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የደቡብ ሱዳንን የአቪዬሽን አገልግሎት ለማሳደግ ቁልፍ ሚና እንዲጫወት ለማድረግ ሲካሄድ የነበረው ውይይት፣ በሁለቱ አገሮች መካከል በተጀመረው አዲስ የኢኮኖሚ ትብብር ውይይት ዳግም መካሄዱ ተገለጸ።

የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ነሐሴ 21 ቀን 2017 ዓ.ም ከኢትዮጵያው የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ ጋር በጁባ መክረዋል። በውይይቱ ወቅትም የደቡብ ሱዳንን የአቪዬሽን ዘርፍ ለማጠናከር እና የቀጠናዊ ትስስርን ለማሳደግ ኢትዮጵያ አየር መንገድ ስትራቴጂካዊ አጋር ሆኖ እንዲያገለግል ሃሳብ መቅረቡን የፕሬዚዳንቱ ጽህፈት ቤት በሰጠው መግለጫ አስታውቋል።

ጽህፈት ቤቱ በመግለጫው፤ “የአየር ትራንስፖርትም በውይይቱ አጀንዳ ውስጥ የተካተተ ሲሆን፣ ኢትዮጵያ አየር መንገድ የደቡብ ሱዳንን የአቪዬሽን አገልግሎት ለማሳደግ እንደ ስትራቴጂያዊ አጋር እንዲሰራ ሃሳብ ቀርቧል” ብሏል። ይሁን እንጂ መግለጫው ከዚህ ውጪ ተጨማሪ ዝርዝር መረጃዎችን አልሰጠም ሲል ሲል የአቪዬሽን ገረገጽ (ch-aviation) ዘግቧል።

በኢትዮጵያ አየር መንገድ እና በደቡብ ሱዳን መካከል የጋራ የንግድ ትብብር ለመፍጠር ውይይት የተጀመረው አ ኤ አ በ 2014 ነበር። በወቅቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈጻሚ የነበሩት አቶ ተወልደ ገብረማርያም፣ አየር መንገዱ በደቡብ ሱዳን የጋራ የንግድ ድርጅት ውስጥ የ49% ድርሻ ለመውሰድ ማቀዱን እና የደቡብ ሱዳን መንግስት ቀሪውን የ51% ድርሻ እንደሚይዝ ተናግረው ነበር።

የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ የተመራ ልዑክ በቅርቡ በጁባ በነበረው በቆይታ ከጠ/ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተላከ መልዕክት ለፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ማደረሱን አዲስ ስታንዳርድ መዘገቡ ይታወሳል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እግዚአብሔር የሰጠኝን ተልዕኮዎች ፈጽሜያለሁ የአዛዥነት ዘመኔ እያበቃ ነው

የኡጋንዳ የመከላከያ ኃይሎች አዛዥ (CDF) ጄነራል ሙሁዚ ካይኔሩጋባ ከወታደራዊ...

አሐዱ ባንክ 1ነጥብ 07 ቢሊዮን ብር አተረፈ

ባንኩ በተጠናቀቀው የሂሳብ ዓመት ከ3 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር...

በጋምቤላ ከምሽት አንድ ሰዓት በኋላ ነዋሪዎች እንዳይንቀሳቀሱ ተከለከለ

ከጋምቤላ ክልል ዋና ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘው ጋምቤላ...

ፍልውሃ እና ሶደሬ!

ከሐዉለት አህመድ በቀደም ከብዙ ዓመታት በኋላ የፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት ሔጄ...