“ዓባይ አፈር ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያን ወርቅ ከተራሮቻችን አጥቦ መውሰዱ ተጨማሪ ቁጭት ነው”

Date:

ዓባይ አፈር ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያን ወርቅ ከተራሮቻችን አጥቦ መውሰዱ ተጨማሪ ቁጭት ነው ሲሉ  ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)  በጉባ ላይ  ባደረጉት ወግ እንደገለጹት፤ ዓባይ ግድብ አሁን ያለውን ቅርጽ የያዘው በየዘመኑ በነበረውና በተነገረው የትርክት ውጤት ነው።

ኢትዮጵያውያንላለፉት ዓመታት እንደ ዓባይ ግድብና መሰል ፕሮጀክቶች የመሥራት መሻት ነበራቸው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ስለዓባይ የተነገሩ ስንኞች፣ ግጥሞች፣ አባባሎች፣ ዘፈኖች እና ጹሁፎች የአሁኑ ትውልድ ስለ ጉዳዩ የደረጀ ሀሳብ እንድይዝ አድርገውታል ብለዋል።

ያኔ ያልሆነበት ምክንያትም የገንዘብ እጥረት፣  የቴክኒክ አቅም ውስንንት እና ጅኦፖለቲክሱ ባለመመቸቱ  መሆኑን ገልጸው፤ አሁን ሊሆን ደግሞ ከጅኦፖለቲክስ ኩስመና ወደተሻለ ቁመና እየተሸጋገርን በመሆኑ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

ዓባይ ለዘመናት የኢትዮጵያን ውሃ፣ አፈር፣ ዓሳ እና ግንዱን ተሸክሞ እንደሚሄድ አንስተው፤ አሁን ላይ የቀረው ደለል ሲፈተሽ ወርቅ እየተገኘበት መሆኑን አስታውቀዋል።

ዓባይ አፈር ብቻ ሳይሆን የኢትዮጽያን ወርቅ ከተራሮቻችን አጥቦ መውሰዱ ተጨማሪ ቁጭት እንድፈጠር ያደርጋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አበባው ደሳለው (ዶ/ር) ከማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲና ተሳትፎ ራሳቸውን አገለሉ

የቀድሞው የተወካዮች ምክር ቤት አባልና የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን)...

ኢትዮጵያ በወጣቶች ኦሊምፒክ አራተኛዋን የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች

በሴኔጋል ዋና ከተማ ዳካር እየተካሄደ ባለው አራተኛው የወጣቶች ኦሊምፒክ...

በወራቤ ሆስፒታል የተመረቀው የኦክስጅን ፋብሪካ በሰዓት 60 ኪዩቢክ ሜትር የማምረት አቅም እንዳለው ተገለጸ

በወራቤ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የተመረቀው የኦክስጅን ማምረቻ ፋብሪካ በሰዓት...