ሁለተኛው የአፍሪካ የአየር ንብረት ጉባዔ (ACS2) ነገ ሰኞ፣ ጳጉሜ 3፣ 2017 ዓ.ም. በአዲስ አበባ እንደሚጀመር የፕላንና ልማት ሚኒስትር አስታዉቋል።
በአዲስ አበባ ዓለም አቀፍ የስብሰባ ማዕከል ለሶስት ቀናት በሚካሄደው በዚህ ጉባዔ ላይ፣ የመንግሥታት እና የክልል መሪዎች፣ ሚኒስትሮች፣ የወጣቶች ተወካዮች፣ የግል ዘርፍ እና የሲቪል ማኅበራት ተሳታፊዎች ይገኛሉ። ጉባዔው “ዓለም አቀፍ የአየር ንብረት መፍትሔዎችን ማፋጠን፦ ለአፍሪካ ጠንካራ እና አረንጓዴ ልማት የገንዘብ ድጋፍ ማድረግ” በሚል መሪ ቃል ይካሄዳል።
የፕላንና ልማት ሚኒስትር እንዲሁም የጉባዔው አስተባባሪ የሆኑት እና ፍፁም አሰፋ ፣ አፍሪካ ለዓለም አቀፍ የካርቦን ልቀት ከ4% በታች አስተዋጽኦ የምታደርግ ቢሆንም፣ ከአየር ንብረት ለውጥ ከፍተኛ ጉዳት እንደምትደርስባት ጠቁመዋል።
በተመሳሳይ፣ አፍሪካ ወጣት ህዝብ ብዛት፣ ከፍተኛ ታዳሽ የኃይል ምንጮች እና የአካባቢ መፍትሔዎችን የመፍጠር አቅም ያላት አህጉር መሆኗን ገልጸዋል።
ጉባዔው በአፍሪካ የሚመሩ መፍትሔዎችን በታዳሽ ኃይል እና በአረንጓዴ ልማት ላይ ማሳየትን እንዲሁም ፍትሃዊ፣ ሊተነበይ የሚችል እና የተስፋፋ የአየር ንብረት ፋይናንስ ለአፍሪካ ቅድሚያ ጉዳዮች እንዲለቀቅ መግፋት ላይ ትኩረት እንደሚያደርግ ተገልጿል።
