ለ9 ቀናት በጃፓን ቶኪዮ ሲካሄድ የቆየው 20ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ትላንት ተጠናቋል፡፡
196 ሀገራት በተሳተፉበት መድረክ 53 ሀገራት ሜዳልያ ሰንጠረጁ ውስጥ የገቡበት ሆኖ አልፏል፡፡ ከአሁን በፊት 46 ሀገራት ሜዳልያ ሰንጠረጁ ውስጥ የገቡት በ2007 የኦሳካ እና በ2023 የቡዳፔስት ዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ሲሆን የቶኪዮው መድረክ በሰባት ሀገራት ብልጫ ያለው ሆኗል፡፡
በሌላ በኩል 619‚288 ተመልካቾች በቶኪዮ ብሔሔዊ ስቴዲየም ተገኝተው ውድድሮቹን ታድመዋል፡፡
20ኛውን የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና አሜሪካ በ16 ወርቅ፣ 5 ብር እና 5 የነሃስ ሜዳልያ በበላይነት ስታጠናቅቅ ኬንያ በ7 ወርቅ፣ 2 ብር 2 ነሀስ 2ኛ እንዲሁም ካናዳ በ3 ወርቅ 1 ብር እና 1 ነሃስ 3ኛ ደረጃን ይዛ ጨርሳለች፡፡
ኢትዮጵያ በ2 ብር እና በ2 የነሃስ ሜዳልያ ከዓለም 22ኛ ደረጃን ይዛ ያጠናቀቀችበት መድረክ ሆኖም ተጠናቋል፡፡
