በኬንያ በተከሰተ የመሬት መንሸራተት አደጋ የሟቾች ቁጥር 26 ደረሰ

Date:

በምዕራብ ኬንያ በተከሰተ ከባድ የመሬት መንሸራተት አደጋ የሟቾች ቁጥር 26 ሲደርስ በቅፅበታዊ ጎርፍ ምክንያት የተረፉ ሰዎችን የመፈለግና የማዳን ሥራ መስተጓጎሉ ተጠቁሟል።

የኬንያ ሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትሩ ኪፕቹምባ ሙርኮመን በአደጋው 25 ሰዎች እስከአሁን የደረሱበት አለመታወቁን ገልፀው ፍለጋውን ተጠናክሮ መቀጠሉ ተናግረዋል።

ቅዳሜ ዕለት በተከሰተው የመሬት መንሸራተት አደጋ መንገዶች ሙሉ በሙሉ በመወሰዳቸው ምክንያት አካባቢው ላይ ለመድረስ እንዲቻል፣ አራት አውሮፕላኖች መሰማራታቸው ተመላክቷል።

በኬንያ ስምጥ ሸለቆ ክልል ውስጥ በምትገኘው ቼሶንጎች አካባቢ ካለ ኮረብታ በተከሰተ ቅፅበታዊ ጎርፍ ምክንያት የፍለጋ ቡድኖች ሥራቸውን በማቋረጥ ቦታውን ለቀው ለመውጣት መገደዳቸውን አሶሼትድ ፕሬስ የዜና ወኪል ዘግቧል።

በኬንያ በተለያዩ አካባቢዎች ከባድ ዝናብ መዝነቡን የቀጠለ ሲሆን፤ የሀገሪቱ መንግሥት ዝናቡ ቀጣይነት ሊኖረው ስለሚችል ለጎርፍ እና ለመሬት መንሸራተት አደጋ ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች የሚኖሩ ሰዎች ወደ አስተማማኝ ቦታ እንዲዘዋወሩ ማሳሰቡን ዘገባው አመልክቷል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እግዚአብሔር የሰጠኝን ተልዕኮዎች ፈጽሜያለሁ የአዛዥነት ዘመኔ እያበቃ ነው

የኡጋንዳ የመከላከያ ኃይሎች አዛዥ (CDF) ጄነራል ሙሁዚ ካይኔሩጋባ ከወታደራዊ...

አሐዱ ባንክ 1ነጥብ 07 ቢሊዮን ብር አተረፈ

ባንኩ በተጠናቀቀው የሂሳብ ዓመት ከ3 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር...

በጋምቤላ ከምሽት አንድ ሰዓት በኋላ ነዋሪዎች እንዳይንቀሳቀሱ ተከለከለ

ከጋምቤላ ክልል ዋና ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘው ጋምቤላ...

ፍልውሃ እና ሶደሬ!

ከሐዉለት አህመድ በቀደም ከብዙ ዓመታት በኋላ የፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት ሔጄ...