ነዋሪዎች የተማረሩበት የዲጂታል ካርታ ጉዳይ

Date:

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በመሬት ይዞታ ጉዳይ በዋናነት ህገወጥነትን ያስቀርልኛል ብሎ ያስተገበረውን ዲጂታል የመሬት ይዞታ ምዝገባ ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ለማግኘት ጥረት ቢያደርጉም አንድ ዓመት ሙሉ እየተጉላሉ መሆኑን ነዋሪዎቹ ቅሬታቸውን ተናግረዋል።

ባለይዞታ ነዋሪዎቹ በተደጋጋሚ “ሲስተም የለም፣ ፋይላችሁ ጠፍቷል፤ ከወር በኋላ ተመለሱ፤” የሚሉና መሰል ምላሾች ከሚኖሩበት ክፍለ ከተማ እንደሚሰጣቸው ገልፀዋል።

“ከእኛ በኋላ የተመዘገቡ ነገር ግን ከእኛ ቅድሚያ ካርታው የተሰራላቸው ሰዎች እንዳሉ እናውቃለን” ያሉ ሲሆን ብልሹ አሰራሮች ማስተዋላቸውን ጠቁመዋል።

አክለውም በዚህ ምክንያት አጥር ማሳጠር ካለመቻል አንስቶ የተለያዩ ቦታዎች ዲጂታል ካርታ ካልያዛችሁ አትስተናገዱም መባላቸውን አስረድተዋል።

የነዋሪዎችን ቅሬታ መነሻ በማድረግ ያናገርነው የመሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ የይዞታ መብት አገልግሎት ዳይሬክተር ሀሰን ሞሳ እንዳሉት አገልግሎቱ አንድ ዓመት ሳይሆን በሦስት ቀናት የሚያልቅ ነው።

የስም ዝውውርንም ሆነ መሰል አገልግሎቶችን ያፋጥናል የተባለው ይህ የካዳስተር ሥራ በተፈለገው ልክ ተግባራዊ እንዲሆን፥ ነዋሪዎች ይዞታቸውን ማስመዝገብ እንዳለባቸውም አስገንዝበዋል።

በጊዜው ካርታ ዲጂታል ማስደረግ ያልቻሉ ዜጎችን በተመለከተም በጊዜ ካርታቸውን ዲጂታል ያላደረጉ ነዋሪዎች አሁን በነፃ የሚሰጠውን የአገልግሎት ወጪውን ራሳቸው እንዲሸፍኑ ይደረጋል ብለዋል።

የዲጂታል ካርታ ተግባራዊነት ህገወጥነት እንዲቀርፍ ታስቦ እንጂ በዚህ ልክ ጊዜ የሚፈጅ አሰራር እንደሌለ የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለምክር ቤት ማስረዳታቸውና፥ በነዋሪዎች የሚነሳው የብልሹ አሰራር ችግር መኖር ምክንያቱ መሆኑን የሚያረጋግጥ ሃሳብ ማጋራታቸው ይታወሳል።

(አራዳ ኤፍ ኤም)

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እግዚአብሔር የሰጠኝን ተልዕኮዎች ፈጽሜያለሁ የአዛዥነት ዘመኔ እያበቃ ነው

የኡጋንዳ የመከላከያ ኃይሎች አዛዥ (CDF) ጄነራል ሙሁዚ ካይኔሩጋባ ከወታደራዊ...

አሐዱ ባንክ 1ነጥብ 07 ቢሊዮን ብር አተረፈ

ባንኩ በተጠናቀቀው የሂሳብ ዓመት ከ3 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር...

በጋምቤላ ከምሽት አንድ ሰዓት በኋላ ነዋሪዎች እንዳይንቀሳቀሱ ተከለከለ

ከጋምቤላ ክልል ዋና ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘው ጋምቤላ...

ፍልውሃ እና ሶደሬ!

ከሐዉለት አህመድ በቀደም ከብዙ ዓመታት በኋላ የፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት ሔጄ...