የኢትዮጵያ የምግብ መሃንዲሶች ማኅበር የምግብ ደህንነትና ዘላቂነትን ለማረጋገጥ እንደሚሰራ ገለጸ

Date:

የኢትዮጵያ የምግብ መሃንዲሶች ማኅበር ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር ሽመልስ አድማሱ ማኅበሩ የምግብ ደህንነት፣ ጥራት እና ዘላቂነትን በማስፈን ግንባር ቀደም መሆኑን ገልጸው፣ በዘርፉ ያለውን ተልዕኮ ለማሳካት ፈጠራና ትብብር ወሳኝ መሆኑን አሳስበዋል።

ፕሬዝዳንቱ እንደገለጹት፣ ዓለም አቀፉ የምግብ ምህንድስና ዘርፍ በቴክኖሎጂ ለውጦች፣ በተጠቃሚዎች ምርጫ እና በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት እየተሻሻለ በመምጣቱ፣ ማኅበሩ ለቀጣዩ ዓመት የሥራ ትኩረቱን በሦስት ቁልፍ ዘርፎች ላይ ማድረጉን አስታውቋል።

የመጀመሪያው ትኩረት ፈጠራና ቴክኖሎጂ ሲሆን፣ እንደ ሰው ሰራሽ አስተውሎት እና የምርት ዕድሜን የሚያራዝሙ የማሸጊያ መፍትሄዎችን የመሳሰሉ ቴክኖሎጂዎችን ወደ ሥራ ማስገባት ነው ብለዋል። ሁለተኛው የችሎታ ግንባታ ሲሆን፣ አባላት በዘርፉ ለሚመጡ ለውጦች ዝግጁ እንዲሆኑ በሥልጠናና ልማት ላይ ኢንቨስት ማድረግ መሆኑን ገልጸዋል።

ሦስተኛውና ደግሞ ትብብር ሲሆን፣ ከዩኒቨርሲቲዎች፣ ከምርምር ተቋማት እና ከኢንዱስትሪ ተዋናዮች ጋር ሽርክናን ማጠናከር መሆኑን አስረድተዋል።

ፕሮፌሰር ሽመልስ የአባላትን ንቁ ተሳትፎ አስፈላጊነት አጽንኦት ሰጥተው፣ ሁሉም አባላት በማኅበሩ ዝግጅቶች ላይ በመገኘት፣ ሃሳባቸውን በማካፈል እና በፕሮጀክቶች ላይ በመተባበር ለኢንዱስትሪው ዕድገት አስተዋፅኦ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።

በመጨረሻም፣በምግብ ምህንድስና የላቀ ደረጃን ለማምጣት በመትጋት፣ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ አስተማማኝ፣ ገንቢ እና ከፍተኛ ጥራት ያለው ምግብ የሚያገኝበትን የወደፊት ጊዜ በጋራ እንገነባለን ተብሏል።

(መናኸሪያ ሬዲዮ)

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አበባው ደሳለው (ዶ/ር) ከማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲና ተሳትፎ ራሳቸውን አገለሉ

የቀድሞው የተወካዮች ምክር ቤት አባልና የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን)...

ኢትዮጵያ በወጣቶች ኦሊምፒክ አራተኛዋን የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች

በሴኔጋል ዋና ከተማ ዳካር እየተካሄደ ባለው አራተኛው የወጣቶች ኦሊምፒክ...

በወራቤ ሆስፒታል የተመረቀው የኦክስጅን ፋብሪካ በሰዓት 60 ኪዩቢክ ሜትር የማምረት አቅም እንዳለው ተገለጸ

በወራቤ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የተመረቀው የኦክስጅን ማምረቻ ፋብሪካ በሰዓት...