የሥነ ልቦና ባለሙያዎች ከዚህ በታች ያሉትን ምልክቶች የሚያሳዩ ሰዎች የዚህ ችግር ያለባቸው መሆናቸውን ይገልጻሉ።
ለረዥም ጊዜ ደስታ ማጣት፣ የመገለል ስሜት፣ ማለዳ እንደነቁ ለቁርስና ለዘወትር የማለዳ ተግባራት ፍላጎት ማጣት፤
በሚያዝናኑ ነገሮች ደስታ ማጣት፣ እንደነቁ ከነገሮች ለመራቅ ስልክን መያዝና በዛ ላይ ጊዜ ማጥፋት፣ ለሚወዱት ነገር ፍላጎት ማጣት፣ ከተለመደው ጊዜ በላይ በሆነ መልኩ የስሜት መቀያየር፤
የበዛ ትኩረት ማጣትና በተደጋጋሚ መርሳት፣ ጥልቅ የፍርሃትና የድካም ስሜት፣ የእንቅልፍ ዑደት መቀያየር፣ የጥፋተኝነት እና ያለመፈለግ ስሜት፣ በተደጋጋሚ የሚከሰት ችግሮች ላይ ብቻ ማተኮርና ያንኑ ደጋግሞ በዐይነ ህሊና መከሰት፤
ንጭንጭና ቁጡ መሆን ብሎም ትዕግስት ማጣት፣ ራስን ለማጥፋትና ሞትን መመኘት፣ ያልተስተካከለ ስሜት መኖር፣ አካላዊና የጤና ለውጥ (በተለይም ራስ ምታትና ሆድ አካባቢ የሚደጋገም የህመም ስሜት) እንዲሁም የየዕለት ሕይወት ላይ የሚከሰት መመሰቃቀል።
እነዚህ ሁኔታዎች ከሳምንት በላይ ለሆነ ጊዜ በየቀኑ የሚታዩ ከሆነ የህክምና ባለሙያ ያማክሩ።
