Date:

ለገዢው ፓርቲ ማጠናከሪያ በመንግስት ተቋማት የሚደረጉ የገንዘብ ማሰባሰቢያዎች “በአስቸኳይ እንዲቆሙ” ኢዜማ ጠየቀ

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ከመንግስት ተቋማት አገልግሎት ጋር በተያያዘ ለገዢው ብልጽግና ፓርቲ ማጠናከሪያ የሚደረግ የገንዘብ ማሰባሰቢያ “በአስቸኳይ ያስቆም” ዘንድ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጥያቄ አቀረበ። ምርጫ ቦርድ በገዢው ፓርቲ ላይ የሚወስደውን “የእርምት እርምጃ” ለህዝብ “በግልጽ እንዲያሳውቅም” ፓርቲው ጠይቋል።

ኢዜማ ትላንት ማክሰኞ መጋቢት 2፤ 2017 ባወጣው መግለጫ፤ ብልጽግና ፓርቲ ባለፈው ጥር ወር መጨረሻ ባካሄደው ጠቅላላ ጉባኤ ካሳለፋቸው ውሳኔዎች አንዱ “ፓርቲውን ማጠናከር” እንደነበር አስታውሷል።

ይህን ተከትሎም ዜጎች “በውድም ሆነ በግድ የፓርቲ ማጠናከሪያ እንዲያዋጡ እየተደረገ” መሆኑን ኢዜማ “ባሰባሰባቸው ማስረጃዎች” ለማወቅ መቻሉን ገልጿል።

በማንኛውም ፓርቲ ያልታቀፉ ግለሰቦች፤ ብልጽግና ፓርቲን ጨምሮ “ለየትኛውም ድርጅት እና በፈቃደኝት የፈለጉትን ድጋፍ የማድረግ መብት እንዳላቸው” እንደሚገነዘብ ኢዜማ አመልክቷል።

ሆኖም ለገዢው ፓርቲ የማጠናከሪያ ገንዘብ እንዲያወጡ እየተገደዱ ያሉት ዜጎች “በተለያዩ የመንግስት ተቋማት ጉዳዮችን ለማስፈጸም በሚንቀሳቀሱበት” ወቅት እንደሆነ ኢዜማ በመግለጫው አብራርቷል።

“ዜጎች አገልግሎት ለማግኘት በሚሄዱባቸው የመንግስታዊ ተቋማት ይህን ተግባር መፈጸም በፍጹም ህገወጥ ተግባር ነው” ሲልም ተቃዋሚ ፓርቲው ነቅፏል።

ብልጽግና ፓርቲ አባላቱ ካልሆኑ ዜጎች “ከመንግሥት ተቋማት አገልግሎት ጋር አያይዞ መዋጮ ማሰባሰብ ምንም ዓይነት የህግም ሆነ የሞራል መሰረት የለውም” ሲልም ተችቷል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የኢትዮጵያ፣ የኤርትራና የህወሓት የቃላት ጦርነት ንሯል።ይዋጉ ይሆን?

ሶስቱም ኃይላት የጦር ኃይላቸዉን እያጠናከሩ፣ አዳዲስ ተዋጊ እየመለመሉ መሆናቸዉ...

የሐማስ ታጣቂዎች ከእስራኤል ጋር በመተባበር የተከሰሱ ሰባት ሰዎችን ገደሉ

ሰኞ እለት በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ እየተዘዋወረ ያለ ቪዲዮ እንደሚያሳየው...