የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሼባ ማይልስ እና አኮያ ፕሮፐርቲስ ስምምነት ተፈራረሙ

Date:

አርቲስት እፀህይወት አበበ የድርጅቱ ብራንድ አምባሳደር ሆነች።

​የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሼባ ማይልስ እና አኮያ ፕሮፐርቲስ የደንበኞቻቸውን ተጠቃሚነት የሚያሳድግ የስትራቴጂካዊ አጋርነት ስምምነት ተፈራርመዋል።

​ታህሳስ 7 ቀን 2018 ዓ.ም በኢትዮጵያ ስካይ ላይት ሆቴል በተከናወነው የፊርማ ስነ-ስርዓት፣ የአየር መንገዱን የሽልማት መርሃ-ግብር (ShebaMiles) ከሪል እስቴት ግብይት ጋር የሚያስተሳስር ስምምነት ተደርጓል።

​​በዚህ ስምምነት መሰረት በአኮያ ፕሮፐርቲስ እየተገነቡ ያሉ ዘመናዊ መኖሪያ ቤቶችን እና የንግድ ሱቆችን የሚገዙ ደንበኞች፣ የስታር አሊያንስ (Star Alliance) አባል ከሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሼባ ማይልስ የጎልድ አባልነት ሽልማት በክብር ያገኛሉ።  ይህም ደንበኞች በኢንቨስትመንታቸው ልክ የአየር መንገዱን ጥቅማጥቅሞች እንዲያገኙ ያስችላቸዋል።

ይህ ስምምነት በኢትዮጵያ አየር መንገድ ሼባ ማይልስ እና የሪል እስቴት ዘርፍ መካከል ያለውን ትብብር ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግር መሆኑ ተመልክቷል።

​በዚሁ መርሃ-ግብር ላይ አኮያ ፕሮፐርቲስ በተለያዩ ፊልሞችና የጥበብ ስራዎቿ ከፍተኛ ተወዳጅነትን ያተረፈችውን አርቲስት እፀህይወት አበበን የድርጅቱ የብራንድ አምባሳደር አድርጎ በይፋ አስተዋውቋል። አርቲስቷ የድርጅቱን ገፅታ በመገንባትና የምርት ስሞቹን ለህዝብ በማስተዋወቅ ረገድ ግንባር ቀደም ስራዎችን እንደምትሰራ ተገልጿል።

​​ከ230 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ እድል የፈጠረው አኮያ ግሩፕ፣ በውስጡ የተለያዩ ታላላቅ ድርጅቶችን አቅፎ የያዘ ግዙፍ ተቋም ነው። ከእነዚህም መካከል፦
📍​አኮያ ፕሮፐርቲስ፦ በሪል እስቴት ዘርፍ ዘመናዊ ቤቶችን የሚያቀርብ፣
📍​አኮያ ኮፊ፦ በቡና ምርትና ኤክስፖርት ላይ የተሰማራ፣
📍​አኮያ ሞተርስ፦ በተሽከርካሪ ግብይት ዘርፍ የሚንቀሳቀሱ ይገኙበታል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እግዚአብሔር የሰጠኝን ተልዕኮዎች ፈጽሜያለሁ የአዛዥነት ዘመኔ እያበቃ ነው

የኡጋንዳ የመከላከያ ኃይሎች አዛዥ (CDF) ጄነራል ሙሁዚ ካይኔሩጋባ ከወታደራዊ...

አሐዱ ባንክ 1ነጥብ 07 ቢሊዮን ብር አተረፈ

ባንኩ በተጠናቀቀው የሂሳብ ዓመት ከ3 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር...

በጋምቤላ ከምሽት አንድ ሰዓት በኋላ ነዋሪዎች እንዳይንቀሳቀሱ ተከለከለ

ከጋምቤላ ክልል ዋና ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘው ጋምቤላ...

ፍልውሃ እና ሶደሬ!

ከሐዉለት አህመድ በቀደም ከብዙ ዓመታት በኋላ የፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት ሔጄ...