በኢትዮጵያ፣ ኬንያና ሶማሊያ እስከ 25 ሚሊየን ሰዎች የምግብ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል

Date:

በአፍሪካ ቀንድ አካባቢ በርካታ ሰዎች ለምግብ ችግር እየተጋለጡ መሆኑና በአካባቢው ከጥቅምት እስከ ታህሳስ የነበረው ደረቅ ወቅትም የእህል ምርት እና የውሃ አማራጭ ላይ ስጋት መፍጠሩ ተነግሯል።

“Famine Early Warning Systems Network( FEWS NET)” በኢትዮጵያ፣ ኬንያና ሶማሊያ ከ20-25 ሚሊየን ሰዎች የሰብዓዊ የምግብ ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው ገልፆ ከግማሽ በላይ ያህሉ በድርቅ የተነሳ መሆኑን ገልጿል።

በአካባቢው አብዛኛው ክፍል የወቅታዊ የዝናብ መጠን ከአማካዩ በ50 በመቶ ያነሰ መሆኑና በአንዳንድ አካባቢዎች ደግሞ ከ30% በታች መሆኑ ተገልጿል።

FEWS NET አብዛኛዎቹ የውሃ አካላት ወደ መድረቅ እና አሳሳቢ ሁኔታ ደርሰዋል ሲል በከፍተኛ ሁኔታ በተጠቁ አካባቢዎች የእፅዋት ሁኔታ ከመደበኛው ወደ 60 በመቶ መቀነሱን ሲገልፅ በጥር እና የካቲትም የሚሰብሰብ ምርት እንደሚቀንስ አስቀምጧል።

የአርብቶ አደር አካባቢዎች በድርቁ ይበልጥ ይፈተናሉ ሲል የእንስሳት የሰውነት ሁኔታ እየቀነሰ መሆኑን ይህም ድርቅን ይቋቋማል በሚባለው ግመል ላይም መታየቱ ተገልጿል።

የግጦሽ መሬት ፍለጋ የሚደረጉ ጉዞዎች በሽታን ከማስፋፋታቸው በተጨማሪ በሶማሊያና ኬንያ ድንበር ላይ ግጭት መፍጠራቸውም ተነግሯል።

ዴይሊ ኔሽን

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ፈንታዬ በላይነህ የቦስተን ግማሽ ማራቶንን ለሦስተኛ ተከታታይ ጊዜ አሸነፈች

በ2026 የቦስተን ግማሽ ማራቶን ውድድር በሴቶች ምድብ ኢትዮጵያዊቷ አትሌት...

ስፖርቲንግ ሊዝበን ለክርስቲያኖ ሮናልዶ እናት እውቅና ሰጠ

የፖርቹጋሉ ክለብ ስፖርቲንግ ሊዝበን ለክርስቲያኖ ሮናልዶ እናት ማሪያ ዶሎሬስ...

በአዲስ አበባ የታክስ ዕዳ ምህረት አሰጣጥን የሚያስተዳድር አዲስ ረቂቅ መመሪያ ወጣ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ቢሮ፣ በተለያዩ ከግብር ከፋዮች...