ከ3 ቢሊዮን ብር በላይ የሕዝብና የመንግሥት ሀብት ከምዝበራ መታደጉ ተገለፀ

Date:



የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ የከተማዋን የ6 ወራት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ባቀረቡበት ወቅት፤ በሕግ የበላይነትን የማስከበር ሂደት 1 ሺህ 382 የፍርድ ቤት መዝገቦች ለአስተዳደሩ እንዲወሰኑ በማድረግ ከ3 ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመት የሕዝብና የመንግሥት ሀብት ከምዝበራ ማዳን ተችሏል ብለዋል።

ይህ ውጤት የተመዘገበው የዐቃቤ ሕግን አቅም በማሳደግና በፍትሕ ሥርዓቱ ላይ በተከናወኑ ጥብቅ የሪፎርም ሥራዎች እንደሆነ ከንቲባዋ አብራርተዋል።

በከተማዋ ሰላማዊ እንቅስቃሴን ለማረጋገጥና የከተማዋን ውበት ለመጠበቅ በተከናወነ የተቀናጀ ዘመቻ፤ ሕገ-ወጥ የመሬት ወረራ፣ ሕገ-ወጥ ግንባታ፣ የጎዳና ላይ ንግድና ሕገ-ወጥ እርድን የመከላከል ተግባር በስፋት መከናወኑን ገልጸዋል።

በዚህ የክትትል ሥራ 101 ቤቶች፣ 19 ሼዶች እና 178 ሔክታር መሬት ሕጋዊነታቸው ተረጋግጦ ወደ መንግሥት ንብረትነት መመለሳቸው ተነግሯል።

ከንቲባዋ አክለውም፤ አዋኪ ድርጊቶችና ሕገ-ወጥ የደረቅና ፍሳሽ አወጋገድ ሥርዓቶችን በመቆጣጠር የከተማዋን ምቾት የመጠበቅ ተግባራት ውጤታማ መሆናቸውን ጠቁመዋል።

የወንጀል ምጣኔን ከመቀነስ አኳያም ከሕገ-ወጥ የጦር መሣሪያና የገንዘብ ዝውውር እንዲሁም ከዝርፊያ ጋር በተያያዘ በርካታ እርምጃዎች ተወስደዋል ተብሏል።

በአገልግሎት አሰጣጥ ረገድም ግልጽ የቅሬታ ማቅረቢያ ሥርዓት በመዘርጋቱ፣ በብልሹ አሠራርና በሌብነት ተግባር ላይ የተሳተፉ 282 ሠራተኞች ላይ አስተዳደራዊና ሕጋዊ እርምጃ መወሰዱ በሪፖርቱ ተመልላክቷል።

በገቢ አሰባሰብ ረገድም በግማሽ ዓመቱ ለመሰብሰብ ከታቀደው 176 ነጥብ 03 ቢሊዮን ብር ውስጥ 162 ነጥብ 72 ቢሊዮን ብር መሰብሰብ ተችሏል። ይህም ከተማዋን በገቢ አሰባሰብና በጀትን በአግባቡ በመጠቀም ረገድ ከአፍሪካ ከተሞች ቀዳሚ እንዲያደርጋትና ልምዷን ለሌሎች እንድታካፍል ማስቻሉ ተገልጿል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አበባው ደሳለው (ዶ/ር) ከማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲና ተሳትፎ ራሳቸውን አገለሉ

የቀድሞው የተወካዮች ምክር ቤት አባልና የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን)...

ኢትዮጵያ በወጣቶች ኦሊምፒክ አራተኛዋን የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች

በሴኔጋል ዋና ከተማ ዳካር እየተካሄደ ባለው አራተኛው የወጣቶች ኦሊምፒክ...

በወራቤ ሆስፒታል የተመረቀው የኦክስጅን ፋብሪካ በሰዓት 60 ኪዩቢክ ሜትር የማምረት አቅም እንዳለው ተገለጸ

በወራቤ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የተመረቀው የኦክስጅን ማምረቻ ፋብሪካ በሰዓት...